ሕዝቅኤል 1:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 እግሮቻቸውም ቀጥ ያሉ እግሮች ነበሩ፥ የእግሮቻቸውም ኮቴ እንደ ጥጃ እግር ኮቴ ነበረ፥ እንደ ተወለወለ ናስም ያንጸባርቅ ነበር። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 እግራቸው ቀጥ ያለ ነበር፤ ኰቴያቸውም እንደ ጥጃ ኰቴ ያለ ሲሆን፣ እንደ ተወለወለ ናስም ያብለጨልጭ ነበር። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 እግራቸው ቀጥ ያለ ሲሆን፥ ውስጥ እግራቸው እንደ ኰርማ ሰኮና ነበር፤ መልካቸውም እንደ ተወለወለ ነሐስ ያበራ ነበር፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 እግሮቻቸውም ቀጥ ያሉ ነበሩ፤ የእግራቸው ሰኰና እንደ ላም እግር ሰኰና ነበረ፤ እንደ ተወለወለ ናስም ይብለጨለጭ ነበር። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 እግሮቻቸውም ቀጥ ያሉ እግሮች ነበሩ፥ የእግራቸውም ኮቴ እንደ ጥጃ እግር ኮቴ ነበረ፥ እንደ ተወለወለ ናስም ይብለጨለጭ ነበር። See the chapter |