ሕዝቅኤል 1:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ ከሰሜን በኩል ዐውሎ ነፋስ መጣ፥ በዙሪያው ብርሃን ያለው መብረቅን የሚረጭ ታላቅ ደመና ነበር፥ በእሳቱም መካከል የሚያንጸባርቅ ነገር ነበረ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 እኔም አየሁ፤ ስመለከትም፣ እነሆ ዐውሎ ነፋስ ከሰሜን በኩል መጣ፤ ይኸውም በታላቅ ብርሃን የተከበበ፣ መብረቅን የሚረጭ ታላቅ ደመና ነበረ፤ የእሳቱም መኻል የጋለ ብረት ይመስል ነበር። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ቀና ብዬ ስመለከት ብርቱ ዐውሎ ነፋስ ከሰሜን በኩል ሲመጣ አየሁ፤ ከግዙፍ ደመና የመብረቅ ብልጭታ ይታይ ነበር፤ በዙሪያው ያለውም ሰማይ ቀላ፤ መብረቁ በሚበርቅበትም ስፍራ አንዳች ነገር እንደ ነሐስ አበራ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 እኔም አየሁ፤ እነሆም ከሰሜን በኩል ዐውሎ ነፋስና ታላቅ ደመና፥ የሚበርቅም እሳት መጣ፤ በዙሪያውም ፀዳል ነበረ፤ በመካከልም በእሳቱ ውስጥ የሚብለጨለጭ ነገር ነበረ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ ከሰሜን በኩል ዐውሎ ነፋስና ታላቅ ደመና የሚበርቅም እሳት መጣ፥ በዙሪያውም ፀዳል ነበረ፥ በመካከልም በእሳቱ ውስጥ እንደሚብለጨለጭ የወርቅ ምስያ ነበረ። See the chapter |