ዘፀአት 9:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ጌታም የፈርዖንን ልብ አጸና፤ ጌታ ሙሴን እንደ ተናገረው ፈርዖን አልሰማቸውም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 እግዚአብሔር ግን የፈርዖንን ልብ አደነደነ፤ እግዚአብሔር ለሙሴ እንደ ተናገረውም፣ ሙሴንና አሮንን መስማት አልፈለገም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ነገር ግን አሁንም እግዚአብሔር የንጉሡን ልብ በማደንደን እግዚአብሔር አስቀድሞ ለሙሴ እንደ ተናገረ ንጉሡ ሙሴንና አሮንን አላደመጣቸውም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 እግዚአብሔርም የፈርዖንን ልብ አጸና፤ እግዚአብሔርም ለሙሴና ለአሮን እንደ ተናገረው አልሰማቸውም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 እግዚአብሔርም የፈርዖንን ልብ አጸና፤ እግዚአብሔር ለሙሴ እንደተናገረው አልሰማቸውም። See the chapter |