ዘፀአት 8:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ጌታም እንደ ሙሴ ቃል አደረገ፤ እንቁራሪቶቹም በየቤቶቹ፥ በየመንደሮቹና በሜዳም ሞቱ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ሙሴም ፈርዖንን፣ “በአባይ ወንዝ ካሉት በቀር ከአንተና ከቤቶችህ ጓጕንቸሮቹ እንዲወገዱ ለአንተ፣ ለሹማምትህና ለሕዝብህ የምንጸልይበትን ጊዜ እንድትወስን ለአንተ ትቼዋለሁ” አለው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ሙሴም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “በደስታ እጸልይልሃለሁ፤ ለአንተና ለመኳንንትህ ለሕዝብህም የምጸልይበትን ሰዓት ብቻ ወስንልኝ፤ ከዚያም በኋላ ጓጒንቸሮቹ ከአንተና ከቤትህ ሁሉ ርቀው በዐባይ ወንዝ ብቻ ተወስነው እንዲኖሩ አደርጋለሁ” አለው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ሙሴም ፈርዖንን፥ “ጓጕንቸሮቹ ከአንተ፥ ከሕዝብህም፥ ከቤቶችህም እንዲጠፉ፥ በወንዙም ብቻ እንዲቀሩ፥ ለአንተ፥ ለሹሞችህም፥ ለሕዝብህም መቼ እንድጸልይ ቅጠረኝ” አለው። ፈርዖንም፥ “ነገ” አለው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ሙሴም ፈርዖንን፥ “ጓጕንቸሮቹ ከአንተም ከቤቶችህም እንዲጠፋ፥ በወንዙም ብቻ እንዲቀሩ፥ ለአንተ ለባሪያዎችህም ለሕዝብህም መቼ እንድጸልይ አስታውቀኝ፤” አለው። See the chapter |