ዘፀአት 6:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ለአብርሃም ለይስሐቅ ለያዕቆብም ሁሉን የሚችል አምላክ ሆኜ ተገለጥኩላቸው፤ ጌታ የሚለውን ስሜን ግን አላስታወቅኳቸውም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ሁሉን ቻይ አምላክ ሆኜ ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅ፣ ለያዕቆብ ተገለጥሁላቸው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በተባለው ስሜ ራሴን አልገለጥሁላቸውም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ሁሉን የምችል አምላክ (ኤልሻዳይ) መሆኔን በማስረዳት ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ተገልጬላቸዋለሁ፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) በተሰኘው ቅዱስ ስሜ አማካይነት ግን አልተገለጥኩላቸውም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ለአብርሃምም፥ ለይስሐቅም፥ ለያዕቆብም ሁሉን እንደሚችል አምላክ ተገለጥሁ፤ ነገር ግን ስሜ እግዚአብሔር አልታወቀላቸውም ነበር። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ለአብርሃምም ለይስሐቅም ለያዕቆብም ሁሉን እንደሚችል አምላክ ተገለጥሁ፤ ነገር ግን ስሜ እግዚአብሔር አልታወቀላቸውም ነበር። See the chapter |