Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፀአት 6:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 እነዚህ ከግብጽ ንጉሥ ከፈርዖን ጋር የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ስለማውጣት የተነጋገሩ ናቸው፤ እነዚህም ሙሴና አሮን ናቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ስለ እስራኤላውያን ከግብጽ መውጣት፣ የግብጽን ንጉሥ ፈርዖንን ያናገሩትም እነዚሁ ሙሴና አሮን ነበሩ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 “የእስራኤልን ሕዝብ ልቀቅ” ብለው ከግብጽ ንጉሥ ጋር የተነጋገሩ እነርሱ ናቸው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 እነ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከግ​ብፅ ያወጡ ዘንድ ከግ​ብፅ ንጉሥ ከፈ​ር​ዖን ጋር የተ​ነ​ጋ​ገሩ ናቸው፤ እነ​ዚ​ህም ሙሴና አሮን ናቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 እነዚህ የእስራኤልን ልጆች “ከግብፅ ያወጡ ዘንድ ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን ጋር የተነጋገሩ ናቸው፤ እነዚህ ሙሴና አሮን ናቸው።

See the chapter Copy




ዘፀአት 6:27
12 Cross References  

ከግብጽ ምድር አውጥቼሃለሁ፥ ከባርነት ቤትም ተቤዥቼሃለሁና፤ በፊትህም ሙሴን፥ አሮንንና ማርያምን ላክሁልህ።


መንገድህ በባሕር ውስጥ ነው፥ ያለፍከውም ኃይለኛ ውኆች በኩል ነው፤ ዱካህ ግን አልታወቀም።


ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “ሂድ፥ አንተ ከግብጽ ምድር ካወጣኸው ሕዝብ ጋር ከዚህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ‘ለዘርህ እሰጣታለሁ’ ብዬ ወደ ማልሁባት ምድር ውጣ፤


ጌታ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከግብጽ ምድር ያወጣኸው ሕዝብህ በድለዋልና ሂድ ውረድ፤


ሙሴና አሮንም ወደ ፈርዖን ሄዱ፥ ጌታም እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ አሮንም በትሩን በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ፊት ጣለ፥ እባብም ሆነ።


እነዚህ አሮንና ሙሴ ጌታ፦ “የእስራኤልን ልጆች በየነገዳቸው ከግብጽ ምድር አውጡ” ያላቸው ናቸው።


ጌታም ሙሴንና አሮንን ተናገራቸው፥ የእስራኤልን ልጆችንና የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንን የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ እንዲያወጣቸው እንዲነግሩት አዘዛቸው።


ጌታ በግብጽ አገር ሙሴን በተናገረው ቀን፥


ሙሴንና አሮንንም ላክሁ፥ በመካከላቸውም እንዳደረግሁ ግብጽን ቀሠፍሁ፤ ከዚያም በኋላ እናንተን አወጣሁ።


ከዚያም ሳሙኤል ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “ሙሴንና አሮንን የመረጠ፥ የቀድሞ አባቶቻችሁንም ከግብጽ ያወጣ ጌታ ነው።


አገልጋዩን ሙሴን የመረጠውንም አሮንን ላከ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements