Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፀአት 39:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ወርቁንም ቀጥቅጠው እንደ ቅጠል ስስ አድርገው እንደ ፈትል ቆረጡት። ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራው በሰማያዊው፥ በሐምራዊው፥ በቀዩ ግምጃ፥ በተፈተለው ጥሩ በፍታ መካከል በእርሱ ጠለፉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ጥበበኛ ባለሙያ እንደሚሠራው በሰማያዊ፣ በሐምራዊ፣ በቀይ ማግና በቀጭን በፍታ ይሠራ ዘንድ ወርቁን በሥሡ ቀጥቅጠው እንደ ክር ቈራረጡት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ወርቁንም ቀጥቅጠው ስስ በማድረግ እንደ ክር አድርገው ቈራረጡት፤ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ከተፈተለም ጥሩ በፍታ ጋር በጥበብ አሠራር ጠለፉት።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ወር​ቁ​ንም ቀጥ​ቅ​ጠው እንደ ቅጠል ስስ አደ​ረ​ጉት፤ እንደ ፈት​ልም ቈረ​ጡት። ብልህ ሠራ​ተ​ኛም እን​ደ​ሚ​ሠራ ሰማ​ያዊ፥ ሐም​ራ​ዊም፥ ቀይ ግም​ጃም፥ የተ​ፈ​ተ​ለም ጥሩ በፍታ፥ ከእ​ርሱ ጠለፉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ወርቁንም ቀጥቅጠው እንደ ቅጠል ስስ አድርገው እንደ ፈትል ቈረጡ። ብልህ ሠራተኛም እንደሚሠራ ሰማያዊ ሐምራዊም ቀይም ግምጃ የተፈተለም ጥሩ በፍታ ከእርሱ ጠለፉ።

See the chapter Copy




ዘፀአት 39:3
6 Cross References  

ሥራ ሲሠሩ ከነበሩት ጥበበኞች የሆኑት ሁሉ ማደሪያውን ሠሩ፤ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ፥ ኪሩቤልም የተጠለፈባቸው ዐሥር መጋረጃዎች ሠሩ።


“ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ የተሠሩ ዐሥር መጋረጆች ያሉበትን ድንኳን ሥራ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤል በእነርሱ ላይ ይሁኑ።


ሰማያዊ፥ ሐምራዊ፥ ቀይ ግምጃ፥ ጥሩ በፍታና የፍየል ጠጉር፥


ኤፉዱንም ከወርቅ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከተፈተለ ጥሩ በፍታ ሠራ።


እንዲጋጠም በሁለቱ ትከሻዎች ላይ መጋጠሚያ ሠሩለት፥ በሁለቱ ጫፎች እንዲጋጠም አደረጉት።


የጢሮስ ሴት ልጅ፥ የምድር ባለ ጠጎች አሕዛብ በፊትሽ ደጅ ይጠናሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements