ዘፀአት 38:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 የአደባባዩ መግቢያ መጋረጃ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከጥሩ በፍታ የተጠለፈ ነበረ፤ ርዝመቱ ሀያ ክንድ፥ ቁመቱ እንደ አደባባዩ መጋረጃዎች አምስት ክንድ ነበረ፤ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 በአደባባዩ መግቢያ ላይ ያለው መጋረጃ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና የጥልፍ ባለሙያ ከጠለፈው፣ በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ የተሠራ ነበር፤ ቁመቱ ሃያ ክንድ፣ እንደ አደባባዩ መጋረጃዎች ከፍታው ዐምስት ክንድ ነበረ፤ See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ወደ ድንኳኑ የሚያስገባው ደጃፍ መጋረጃ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ በፍታ ተፈትሎ በእጅ ጥበብ ካጌጠ ቀጭን ሐር የተሠራ ነበር፤ እርሱም እንደ ድንኳኑ በር መግቢያ መጋረጃዎች ሁሉ ርዝመቱ ዘጠኝ ሜትር ቁመቱም ሁለት ሜትር ነበር፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 የአደባባዩም ደጅ መጋረጃ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይም ግምጃ ፥ ከጥሩም በፍታ በጥልፍ አሠራር የተሠራ ነበረ፤ ርዝመቱ ሃያ ክንድ ነበረ፤ ቁመቱም እንደ አደባባዩ መጋረጃዎች አምስት ክንድ ነበረ፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 የአደባባዩም ደጅ መጋረጃ ከሰማያዊ ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ፥ ከጥሩም በፍታ በጥልፍ አሠራር የተሠራ ነበረ፤ ርዝመቱ ሀያ ክንድ ነበረ፥ ቁመቱም እንደ አደባባዩ መጋረጆች አምስት ክንድ ነበረ፤ See the chapter |