Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፀአት 37:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በአንደኛው ቅርንጫፍ እንቡጥ፥ ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች፥ በሁለተኛውም ቅርንጫፍ እንቡጥ፥ ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች፥ እንዲሁም ከመቅረዙ ለወጡ ለስድስቱ ቅርንጫፎች አደረገ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ከእንቡጦችና ከፈኩ አበቦች ጋራ የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች በአንዱ ቅርንጫፍ ላይ፣ ሦስቱ ደግሞ በሚቀጥለው ቅርንጫፍ ላይ ነበሩ፤ ከመቅረዙ ለወጡት ለስድስቱም ቅርንጫፎች ሁሉ እንዲሁ ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ስድስቱም ቅርንጫፎች እያንዳንዱ እንቡጥና ቀንበጥ ያላቸውን የለውዝ አበባዎችን የሚመስሉ ሦስት ሦስት ጌጠኛ የአበባ ወርድ ተስለውበት ነበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 በአ​ን​ደ​ኛው ቅር​ን​ጫፍ ጕብ​ጕ​ቡ​ንና አበ​ባ​ውን፥ ሦስ​ትም የለ​ውዝ አበባ የሚ​መ​ስ​ሉ​ትን ጽዋ​ዎች፥ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቅር​ን​ጫፍ ጕብ​ጕ​ቡ​ንና አበ​ባ​ውን፥ ሦስ​ትም የለ​ውዝ አበባ የሚ​መ​ስ​ሉ​ትን ጽዋ​ዎች፥ እን​ዲ​ሁም ከመ​ቅ​ረ​ዝዋ ለወጡ ለስ​ድ​ስቱ ቅር​ን​ጫ​ፎች አደ​ረገ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 በአንደኛው ቅርንጫፍ ጕብጕቡንና አበባውን ሦስትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች፥ በሁለተኛውም ቅርንጫፍ ጕብጕቡንና አበባውን ሦስትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች፥ እንዲሁም ከመቅረዙ ለወጡ ለስድስቱ ቅርንጫፎች አደረገ።

See the chapter Copy




ዘፀአት 37:19
3 Cross References  

በአንደኛው ቅርንጫፍ እንቡጥና ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች፥ በሁለተኛውም ቅርንጫፍ እንቡጥና ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች አድርግ፤ እንዲሁም ከመቅረዙ ለሚወጡ ለስድስቱ ቅርንጫፎች አድርግ።


በጎኑም ስድስት ቅርንጫፎች ወጡለት፤ ሦስቱ የመቅረዙ ቅርንጫፎች በአንድ በኩል፥ ሦስቱም የመቅረዙ ቅርንጫፎች በሌላ በኩል።


በመቅረዙም ጉብጉቦቹንና አበቦቹን አራትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች አደረገ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements