Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፀአት 36:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ከሃያው ሳንቃዎች በታች አርባ የብር እግሮችን አደረገ፤ በአንደኛው ሳንቃ ለሁለቱ ማጋጠሚያዎች ሁለት እግሮች፥ በሁለተኛው ሳንቃ ለሁለቱ ማጋጠሚያዎች ሁለት እግሮች አደረገ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ለእያንዳንዱ ጕጠት አንድ መቆሚያ፣ ለእያንዳንዱም ወጋግራ ሁለት መቆሚያ ሆኖ አርባ የብር መቆሚያዎችን አበጁ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ከኻያውም ተራዳዎች በታች ሁለት ማገጣጠሚያ ጒጦች ባሉት በእያንዳንዱ ተራዳ ሥር ሁለት ሁለት በማኖር አርባ የብር እግሮችን አደረጉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ከሃ​ያ​ውም ሳን​ቆች በታች አርባ የብር እግ​ሮች አደ​ረጉ፤ ከእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሳንቃ በታች ለሁ​ለቱ ማጋ​ጠ​ሚ​ያ​ዎች ሁለት እግ​ሮች ነበሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ከሀያውም ሳንቆች በታች አርባ የብር እግሮች አደረጉ፤ ከእያንዳንዱም ሳንቃ በታች ለሁለቱ ማጋጠሚያዎች ሁለት እግሮች ነበሩ።

See the chapter Copy




ዘፀአት 36:24
4 Cross References  

ከሀያውም ሳንቃዎች በታች አርባ የብር እግሮችን አድርግ፤ ከእያንዳንዱ ሳንቃ በታች ለሁለት ማጋጠሚያዎች ሁለት እግሮች ይሁኑ።


ለማደሪያው ሳንቃዎችን አደረገ፤ በደቡብ በኩል ሃያ ሳንቃዎችን አደረገ፤


ለማደሪያው ለሁለተኛው ወገን በሰሜን በኩል ሃያ ሳንቃዎችን አደረገ፤


ለእያንዳንዱም ሳንቃ አንዱን በአንዱ ላይ የሚያያይዙ ሁለት ማጋጠሚያዎች ይሁኑለት፤ ለማደሪያው ሳንቃዎች ሁሉ እንዲሁ አድርግ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements