Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፀአት 34:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 አሮንና የእስራኤል ልጆች ሁሉ ሙሴን ባዩ ጊዜ፥ እነሆ ፊቱ ያንጸባርቅ ነበር፥ ወደ እርሱ ለመቅረብ ፈሩ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 አሮንና እስራኤላውያን ሁሉ ሙሴን ባዩት ጊዜ ፊቱ ያበራ ነበር፤ ወደ እርሱ ለመቅረብም ፈርተው ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 አሮንና ሕዝቡ ሁሉ ሙሴን ባዩ ጊዜ ፊቱ እንደሚያበራ ተመልክተው ወደ እርሱ ለመቅረብ ፈሩ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 አሮ​ንና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ እነሆ፥ ፊቱ እን​ዳ​ን​ጸ​ባ​ረቀ ሙሴን በአዩ ጊዜ፥ ወደ እርሱ ለመ​ቅ​ረብ ፈሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 አሮንና የእስራኤል ልጆች ሁሉ ሙሴን ባዩ ጊዜ፥ እነሆ የፊቱ ቁርበት አንጸባረቀ፤ ወደ እርሱም ይቀርቡ ዘንድ ፈሩ።

See the chapter Copy




ዘፀአት 34:30
7 Cross References  

ልብሱም በምድር ላይ ማንም አጣቢ አጥቦ ሊያነጣው በማይችልበት ሁናቴ እጅግ ነጭ ሆነ።


ስምዖን ጴጥሮስም ይህን ባየ ጊዜ በኢየሱስ ጉልበት ፊት ወድቆ፦ “ጌታ ሆይ! እኔ ኀጢአተኛ ሰው ነኝና ከኔ ራቅ፤” አለው።


ሕዝቡ ሁሉ ሲያዩት ወዲያው ተደንቀው እጅ ሊነሡት ወደ እርሱ ሮጡ።


እኔ በምሳሌ ሳይሆን እፊት ለፊት ከእርሱ ጋር በግልጥ እነጋገራለሁ፤ የጌታንም ሀልዎተ-ቅርፅ ይመለከታል፤ ታዲያ፥ በባርያዬ በሙሴ ላይ ለመናገር ለምን አልፈራችሁም?”


ዳሩ ግን የእስራኤል ልጆች ስለዚያ ስለ ተሻረው፥ ስለ ፊተኛው ክብር የሙሴን ፊት ትኩር ብለው መመልከት እስኪሳናቸው ድረስ፥ ያ በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸ የሞት አገልግሎት ያን ያህል ክቡር ከሆነ፥


ሙሴ ግን ጠራቸው፥ አሮንና የማኅበሩ አለቆች ሁሉ ወደ እርሱ ተመለሱ፤ ሙሴም አነጋገራቸው።


ጠቢብን የሚመስለው? የነገሮችንስ ትርጒም የሚያውቅ ማን ነው? የሰው ጥበብ ፊቱን ታበራለች፥ የፊቱንም ድንዳኔ ትለውጣለች።


Follow us:

Advertisements


Advertisements