ዘፀአት 34:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)29 ሙሴ ከሲና ተራራ በሚወርድበት ጊዜ እንዲህ ሆነ፥ ሁለቱ የምስክር ጽላቶች ከተራራው በሚወርድበት ጊዜ በሙሴ እጅ ነበሩ፤ ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ስለ ተነጋገረ ፊቱ እንዳንጸባረቀ አላወቀም ነበር። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም29 ሙሴ ሁለቱን የምስክር ጽላት በእጆቹ ይዞ ከሲና ተራራ በወረደ ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋራ ከመነጋገሩ የተነሣ ፊቱ እንደሚያበራ አላወቀም ነበር። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም29 ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገር ቈይቶ ስለ ነበር፥ ዐሥሩ ትእዛዞች የተጻፉባቸውን ሁለቱን የምስክር ጽላቶች ይዞ ከሲና ተራራ በወረደ ጊዜ ፊቱ አበራ፤ ለእርሱ ግን ይህ ሁሉ አይታወቀውም ነበር። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)29 እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ ከሲና ተራራ በወረደ ጊዜ ሁለቱ ጽላት በሙሴ እጅ ነበሩ፤ ሙሴም ከተራራው በወረደ ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገር ፊቱ እንዳንጸባረቀ አላወቀም ነበር። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)29 እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ ከሲና ተራራ በወረደ ጊዜ ሁለቱ የምስክር ጽላቶች በሙሴ እጅ ነበሩ፤ ሙሴም ከተራራው በወረደ ጊዜ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለ ተነጋገረ የፊቱ ቁርበት እንዳንጸባረቀ አላወቀም ነበር። See the chapter |