ዘፀአት 33:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ሙሴ ጌታን እንዲህ አለው፥ “እይ! አንተ ‘ይህን ሕዝብ አውጣ’ ብለኸኛል፥ ነገር ግን ከእኔ ጋር የምትልከውን አላስታወቅኸኝም። አንተም፦ ‘በስምህ አወቅሁህ፥ ደግሞም በእኔ ፊት ሞገስን አግኝተሃል’ ብለኸኝ ነበር። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 ሙሴ እግዚአብሔርን አለው፤ “ ‘እነዚህን ሕዝብ ምራ’ ብለህ ነግረኸኝ ነበር፤ ከእኔ ጋራ የምትልከው ማን እንደ ሆነ ግን አላሳወቅኸኝም፤ ‘አንተን በስም ዐውቅሃለሁ፤ በፊቴም ሞገስ አግኝተሃል’ ብለህ ነበር። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ሙሴም እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፦ “ይህን ሕዝብ ወደዚያች ምድር መርቼ እንድወስድ አዝዘኸኛል፤ ነገር ግን ከእኔ ጋር ማንን እንደምትልክ አልነገርከኝም፤ እኔን እንደምታውቀኝና በእኔም ደስ እንደሚልህ ገልጠህልኛል፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 ሙሴም እግዚአብሔርን፥ “እነሆ፥ አንተ፦ ይህን ሕዝብ አውጣ ትለኛለህ፤ ነገር ግን ከእኔ ጋር የምትልከውን አላስታወቅኸኝም። አንተም ከሁሉ ይልቅ ዐወቅሁህ፥ ደግሞም በእኔ ፊት ሞገስን አገኘህ አልኸኝ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 ሙሴም እግዚአብሔርን፦ እነሆ አንተ፦ ይህን ሕዝብ አውጣ ትለኛለህ፤ ከእኔም ጋር የምትልከውን አላስታወቅኸኝም። አንተም፦ በስምህ አወቅሁህ፥ ደግሞም በእኔ ፊት ሞገስን አገኘህ አልኸኝ። See the chapter |