ዘፀአት 32:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 እኔም፦ ‘ከእናንተ ወርቅ ያለው ሰው ሁሉ ሰብሮ ያምጣልኝ’ አልኋቸው፤ እነርሱም ሰጡኝ፥ በእሳት ላይ ጣልሁት፥ ይህም ጥጃ ወጣ።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 ስለዚህ፣ ‘ማንኛውም ዐይነት የወርቅ ጌጣጌጥ ያለው ሁሉ ያውልቀው’ አልኋቸው፤ ከዚያም ወርቁን ሰጡኝ፤ ወደ እሳቱ ጣልሁት፤ ይህም ጥጃ ወጣ።” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 እኔ ከወርቅ የተሠሩ ጌጣጌጦቻቸውን አውልቀው እንዲያመጡልኝ ነገርኳቸው፤ እነርሱም ያላቸውን ጌጣጌጥ ሁሉ አመጡልኝ፤ ጌጣጌጦቹንም ወደ እሳት ውስጥ በጣልኳቸው ጊዜ ይህ የጥጃ ምስል ወጣ።” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 እኔም ከእናንተ ወርቅ ያለው ሰው ያምጣልኝ አልኋቸው፤ ሰጡኝም፤ በእሳትም ላይ ጣልሁት፤ ይህም ጥጃ ወጣ።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 እኔም፦ ከእናንተ ወርቅ ያለው ሰው ከእርሱ ሰብሮ ያምጣልኝ አልኋቸው፤ ሰጡኝም፤ በእሳትም ላይ ጣልሁት፥ ይህም ጥጃ ወጣ። See the chapter |