Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፀአት 30:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከአክሊሉ በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን አድርግለት፤ በዚህና በዚያ በሁለቱ ጎን ታደርጋቸዋለህ፤ በእነርሱ እንዲሸከሙም የመሎጊያዎቹ ማስገቢያ ይሁኑ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 መሠዊያውን ለመሸከም የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች የሚይዙ፣ ከክፈፉ በታች ትይዩ የሆኑ ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ለመሠዊያው አብጅ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተህ መሠዊያውን ለመሸከም የሚያገለግሉት መሎጊያዎች እንዲገቡበት ከክፈፉ ሥር አያይዛቸው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከክ​ፈ​ፉም በታች ሁለት የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶች አድ​ር​ግ​ለት። በዚ​ህና በዚያ በሁ​ለቱ ጐን ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ፤ እር​ሱን ያነ​ሡ​ባ​ቸው ዘንድ የመ​ሎ​ጊ​ያ​ዎቹ መግ​ቢያ ይሁኑ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ከክፈፉም በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶች አድርግለት። በዚህና በዚያ በሁለቱ ጎን ታደርጋቸዋለህ፤ ለመሸከምም የመሎጊያዎች ስፍራ ይሁኑ።

See the chapter Copy




ዘፀአት 30:4
8 Cross References  

ገበታውንም ለመሸከም መሎጊያዎቹ እንዲሰኩባቸው ቀለበቶቹ በክፈፉ አቅራቢያ ይሁኑ።


መሎጊያዎቹ በቀለበቶቹ ውስጥ ይግቡ፥ መሠዊያውን ለመሸከም መሎጊያዎቹ በሁለቱ ጎኖች ይሁኑ።


እንደ መረብ ሆኖ የተሠራ የነሐስ መከታ አድርግለት፤ ለመከታውም አራት የነሐስ ቀለበት በአራቱም ማዕዘን አድርግለት።


ሳንቆቹንም በወርቅ ለብጣቸው፥ ቀለበቶቻቸውንም የመወርወሪያ ቤት እንዲሆኑላቸው ከወርቅ ሥራቸው፥ መወርወሪያዎችንም በወርቅ ለብጣቸው።


ታቦቱን በእነርሱ ለመሸከም በታቦቱ ጎን ባሉት ቀለበቶች መሎጊያዎቹን አስገባ።


አራት የወርቅ ቀለበቶችም አድርግለት፥ እነርሱንም በአራቱ እግሮቹ ላይ አኑር፤ በአንድ ወገን ሁለት ቀለበቶች፥ በሌላው ወገን ሁለት ቀለበቶች ይሁኑ።


ላዩን፥ የጎኖቹን ዙሪያ ሁሉና ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ትለብጠዋለህ፤ ዙሪያው የወርቅ አክሊል ታደርግለታለህ።


መሎጊያዎቹን ከግራር እንጨት ሠርተህ በወርቅ ለብጣቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements