Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፀአት 30:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ለነፍሳችሁ ማስተስረያ የጌታን ስጦታ ስትሰጡ፥ ከግማሽ ሰቅሉ ባለ ጠጋው አይጨምር፥ ደሃውም አያጉድል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ለሕይወታችሁ ማስተስረያ እንዲሆን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት በምታቀርቡበት ጊዜ ባለጠጋው ከግማሽ ሰቅል በላይ፣ ድኻውም አጕድሎ አይስጥ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ለሕይወታቸው ቤዛ ይህን መባ ሲያቀርቡ ሀብታሙም ሆነ ድኻው እኩል ይክፈል እንጂ የሀብታሙ ክፍያ ብዙ የድኻው ክፍያ አነስተኛ አይሁን።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ለነ​ፍ​ሳ​ችሁ ቤዛ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስጦታ ስት​ሰጡ ባለ ጠጋው ከሰ​ቅል ግማሽ አይ​ጨ​ምር፤ ድሃ​ውም አያ​ጕ​ድል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ለነፍሳችሁ ማስተስረያ የእግዚአብሔርን ስጦታ ስትሰጡ ባለ ጠጋው ከሰቅል ግማሽ አይጨምር፥ ደሀውም አያጉድል።

See the chapter Copy




ዘፀአት 30:15
12 Cross References  

ሰውም ሁሉ ካገኘው ከወርቅ ዕቃ፥ ከእግር አልቦም፥ ከአምባርም፥ ከቀለበትም፥ ከጉትቻም፥ ከወርቁም ጌጣጌጥ ለነፍሳችን በጌታ ፊት እንዲያስተሰርይልን ለጌታ መባ አምጥተናል።”


እናንተም ጌቶች ሆይ! ዛቻውን ትታችሁ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ በእነርሱና በእናንተ ላይ የሚገዛው ጌታ በሰማይ እንዳለ ለሰው ፊትም እንደማያዳላ ታውቃላችሁ።


እነርሱ ሁሉ የእጁ ሥራ ናቸውና ለአለቆች አያደላም፥ ሀብታሙንም ሰው ከድሀው ይበልጥ አይመለከትም።


የሥጋ ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና፤ ደሙም ከሕይወቱ የተነሣ ያስተሰርያልና በመሠዊያው ላይ ለነፍሳችሁ ማስተስረያ እንዲሆን እኔ ለእናንተ ሰጠሁት።


“አንተ የእስራኤልን ልጆች ቍጥር ተቀብለህ በቆጠርሃቸው ጊዜ መቅሰፍት እንዳይሆንባቸው፥ በቆጠርሃቸው ጊዜ ከእነርሱ ሰው ሁሉ እንደ ቁጥራቸው መጠን የነፍሱን ቤዛ ለእግዚአብሔር ይስጥ።


የሚበድልም እንደ በደሉ መጠን ብድራቱን ይቀበላል፤ ለሰው ፊትም አድልዎ የለምና።


ሀብታምና ድሀ ይገናኛሉ፥ ሁለቱንም የፈጠራቸው ጌታ ነው።


ዳዊትም ገባዖናውያንን፥ “ምን ላድርግላችሁ? የጌታን ርስት ትባርኩ ዘንድ ማስተሰረያውን ምን ማድረግ አለብኝ?” ሲል ጠየቃቸው።


በዚህ ቆጠራ የሚያልፍ፥ ሃያ ዓመት የሞላውና ከዚያም በላይ የሆነ ሁሉ፥ ይህንን ስጦታ ለጌታ ይስጥ።


የማስተስረያውን ገንዘብ ከእስራኤል ልጆች ወስደህ ለመገናኛው ድንኳን አገልግሎት ስጠው፤ ለእስራኤል ልጆች ለነፍሳችሁ ቤዛ እንዲሆን በጌታ ፊት መታሰቢያ ይሆናል።”


በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት፥ የሰቅል ግማሽ ከተቆጠረው ከእያንዳንዱ ሰው የተሰጠ ነው፤ ይህም ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያ በላይ የተቆጠሩት ሁሉ ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ አምሳ ሰዎች ነበሩ።


የምድሪቱም ሕዝብ ሁሉ ይህን መባ ለእስራኤል መሪ ይሰጣሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements