ዘፀአት 30:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 በቆጠራው የሚያልፉ ሁሉ ይህን ይስጡ፥ በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት ግማሽ ሰቅል ይሰጣል፥ ሰቅል ሃያ ጌራ ነው፤ ግማሽ ሰቅል ለጌታ ስጦታ ነው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ማንም ወደ ተቈጠሩት ዘንድ የሚያልፍ ሃያ አቦሊ በሚመዝን በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን ግማሽ ሰቅል መስጠት አለበት፤ ይህ ግማሽ ሰቅል ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት ነው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ከሕዝብ ቈጠራ ውስጥ የሚገባ እያንዳንዱ ሰው በተቀደሰው ድንኳን በታወቀው ሚዛን ልክ አንድ ጥሬ ብር ይክፈል፤ እያንዳንዱ ሰው ይህን ለእግዚአብሔር መባ አድርጎ ያቅርብ፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 ይቈጠሩ ዘንድ የሚያልፉት ሁሉ የሚሰጡት ይህ ነው፤ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን የሰቅል ግማሽ ይሰጣል። ሰቅሉም ሃያ አቦሊ ነው፤ የሰቅሉም ግማሽ ለእግዚአብሔር ቍርባን ነው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 አልፎ የሚቆጠር ሁሉ ግማሽ ሰቅል እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ይሰጣል፤ የሰቅል ግማሽ ለእግዚአብሔር ያነሣል። See the chapter |