ዘፀአት 30:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 አሮን በዓመት አንድ ጊዜ በቀንዶቹ ላይ ማስተስረያ ያደርጋል፤ በዓመት አንድ ጊዜ ለትውልዳችሁ ማስተስረያ በሚሆን በኃጢአት መሥዋዕት ደም ማስተስረያ ያደርግበታል። ለጌታ እጅግ የተቀደሰ ነው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 አሮን በዓመት አንድ ጊዜ በቀንዶቹ ላይ ማስተስረያ ያደርግበታል፤ ይህ ዓመታዊ ማስተስረያ በሚመጡት ትውልዶች ሁሉ ለማስተስረያ ከሚሆን የኀጢአት መሥዋዕት ደም ጋራ መደረግ አለበት፤ ይህም ለእግዚአብሔር እጅግ ቅዱስ ነው።” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 አሮን በዓመት አንድ ጊዜ ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ከታረደው እንስሳ ደም ወስዶ በአራቱም ጒጦች ላይ በማድረግ መሠዊያው የሚነጻበትን ሥርዓት ይፈጽም፤ ይህም ሥርዓት በሚመጡት ዘመናት ሁሉ በየዓመቱ ይፈጸም፤ በዚህ ዐይነት ይህ መሠዊያ ለእግዚአብሔር በፍጹም የተቀደሰ ይሁን።” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 አሮንም በዓመት አንድ ጊዜ በቀንዶቹ ላይ ማስተስረያ ያደርጋል፤ በዓመት አንድ ጊዜ ኀጢአትን ከሚያነጻው ደም ይወስዳል፤ የልጅ ልጆቻቸውንም እንዲያነጻ ያደርጋል፤ ይህም ለእግዚአብሔር ቅዱሰ ቅዱሳን ነው።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 አሮንም በአመት አንድ ጊዜ በቀንዶቹ ላይ ማስተስረያ ያደርጋል፤ በአመት አንድ ጊዜ ለልጅ ልጃችሁ ማስተስረያ በሚሆን በኃጢአት መሥዋዕት ደም ማስተስረያ ያደርግበታል። ለእግዚአብሔር ቅድስተ ቅዱሳን ናት። See the chapter |