ዘፀአት 29:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 አውራውን በግ በሙሉ በመሠዊያው ላይ ታቃጥለዋለህ፤ ለጌታ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው፤ ጣፋጭ ሽቱ ነው፤ ለጌታ የቀረበ የእሳት ቁርባን ነው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ከዚያም አውራ በጉን በሙሉ በመሠዊያው ላይ አቃጥለው፤ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ጣፋጭ መዐዛና ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ነው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ከዚያም በኋላ የአውራውን በግ ሥጋ በሙሉ ለእኔ ለእግዚአብሔር የምግብ መሥዋዕት አድርገህ አቃጥለው፤ ይህም መባ ሽታው እኔን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 አውራንም በግ በሞላው በመሠዊያው ላይ ታቃጥላለህ፤ ስለ ጣፋጭ ሽታ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነው፤ ለእግዚአብሔር የቀረበ የእሳት ቍርባን ነው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 አውራውንም በግ በሞላው በመሠዊያው ላይ ታቃጥላለህ፤ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነው፤ ጣፋጭ ሽቱ ነው። ለእግዚአብሔር የቀረበ የእሳት ቍርባን ነው። See the chapter |