ዘፀአት 28:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)39 እጀ ጠባቡን ከጥሩ በፍታ፥ መጠምጠሚያውን ከበፍታ ትሠራለህ፥ በጥልፍ የተጠለፈ መታጠቂያ ትሠራለህ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም39 “ሸሚዙን ከቀጭን በፍታ ሥራ፤ መጠምጠሚያውንም ከቀጭን በፍታ አብጀው፤ መታጠቂያውንም ጥልፍ ጠላፊ የሠራው ይሁን። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም39 “የአሮንን ሸሚዝና መጠምጠሚያ ከጥሩ በፍታ ሥራው፤ መታጠቂያውም ከጥሩ በፍታ ተሠርቶ በጥልፍ ጥበብ ያጌጠ ይሁን። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)39 ቀሚሱንም ከጥሩ በፍታ ዝንጕርጕር አድርገህ፥ አክሊልን ከበፍታ ትሠራለህ፤ በጥልፍ አሠራርም መታጠቂያ ትሠራለህ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)39 ሸሚዙንም ከጥሩ በፍታ ዝንጕርጕር አድርገህ፥ መጠምጠሚያውን ከበፍታ ትሠራለህ፤ በጥልፍ አሠራር መታጠቂያም ትሠራለህ። See the chapter |