ዘፀአት 28:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ካህን ሆኖ እንዲያገለግለኝ የተለየ እንዲሆን ለአሮን ልብስ እንዲሠሩለት የጥበብ መንፈስ ለሞላሁባቸው በልባቸው ጥበበኞች ለሆኑት ሁሉ ተናገር። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ካህን ሆኖ እንዲያገለግለኝ የተለየ ይሆን ዘንድ ጥበብ ለሰጠኋቸው በዚህ ጕዳይ ላይ ጥበበኛ ለሆኑ ሰዎች ሁሉ ለአሮን መጐናጸፊያዎችን እንዲሠሩለት ንገራቸው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 እኔ ልዩ ችሎታ እንዲኖራቸው ያደረግኋቸውን የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎችን ጠርተህ ለአሮን ልብስ እንዲሠሩለት ንገራቸው፤ በዚህ ዐይነት አሮን ካህን በመሆን ያገለግለኝ ዘንድ ለእኔ የተለየ ይሆናል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 አንተም የጥበብ መንፈስ ለሞላሁባቸው፥ በልባቸው ጥበበኞች ለሆኑት ሁሉ ተናገር። እነርሱም ካህን ሆኖ እንዲያገለግለኝ ለአሮን ለቤተ መቅደስ የሚሆን የተለየ ልብስ ይሥሩ፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 አንተም ካህን ሆኖ እንዲያገለግለኝ አሮን ቅዱስ ይሆን ዘንድ ልብስ እንዲሠሩለት የጥበብ መንፈስ ለሞላሁባቸው በልባቸው ጥበበኞች ለሆኑት ሁሉ ተናገር። See the chapter |