ዘፀአት 26:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ማደሪያውን እንዲሸፍን ከርዝመቱ በአንድ ወገን አንድ ክንድ፥ በአንድ ወገንም አንድ ክንድ ከድንኳኑ መጋረጆች የቀረው ትርፍ በማደሪያው ውጭ በወዲህና በወዲያ ይንጠልጠል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 የድንኳኑ መጋረጃዎች በሁለቱም ጐኖች አንድ ክንድ ርዝመት ይኖራቸዋል፤ የተረፈውም የማደሪያውን ድንኳን ጐኖች እንዲሸፍን ሆኖ ይንጠለጠላል፤ See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 በርዝመቱ በኩል ከእያንዳንዱ መጋረጃ ትርፍ ሆነው የቀሩት ግማሽ ሜትር ስፋት ያላቸው መጋረጃዎች በጐንና ጐን ተንጠልጥለው ድንኳኑን ይሸፍኑት። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 ድንኳኑን እንዲሸፍን ከርዝመቱ በአንድ ወገን አንድ ክንድ፤ በአንድ ወገንም አንድ ክንድ ከድንኳኑ መጋረጆች የቀረው ትርፍ በድንኳኑ ውጭ በወዲህና በወዲያ ይጋረድ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 ማደሪያውን እንዲሸፍን ከርዝመቱ በአንድ ወገን አንድ ክንድ፥ በአንድ ወገንም አንድ ክንድ ከድንኳኑ መጋረጆች የቀረው ትርፍ በማደሪያው ውጭ በወዲህና በወዲያ ይንጠልጠል። See the chapter |