ዘፀአት 22:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 አንድ ሰው ብር ወይም ሌላ ነገር እንዲጠብቅለት ለባልንጀራው በአደራ ቢሰጥ፥ ከቤቱም ቢሰረቅና ሌባው ቢገኝ እጥፍ ይክፈል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 “እሳት ተነሥቶ ወደ ቍጥቋጦ ቢዘምትና ክምርን ወይም ያልታጨደን እህል ወይም አዝመራውን እንዳለ ቢበላ፣ እሳቱን ያቀጣጠለው ሰው ካሳ ይክፈል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 “አንድ ሰው በእርሻው ውስጥ እሳት ቢያቀጣጥልና እሳቱ በቊጥቋጦ ተላልፎ ወደ ሌላው ሰው እርሻ በመዛመት በማደግ ላይ ያለውንም ሆነ ታጭዶ የተከመረውን እህል ቢያቃጥል፥ እሳቱን ያቀጣጠለው ሰው ካሣ ይክፈል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 “እሳት ቢነሣ ጫካውንም ቢይዝ፥ ዐውድማውንም፥ ክምሩንም ወይም ያልታጨደውን እህል ወይም እርሻውን ቢያቃጥል እሳቱን ያነደደው ይክፈል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 እሳት ቢነሣ፥ እሾኽንም ቢይዝ፥ ክምሩንም ወይም ያልታጨደውን እህል ወይም እርሻውን ቢያቃጥል፥ እሳቱን ያነደደው ይካስ። See the chapter |