ዘፀአት 22:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 እግዚአብሔርን አትስደብ፥ የሕዝብህንም መሪ አትርገም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም27 ምክንያቱም ለሰውነቱ መሸፈኛ ያለው ልብስ ያ ብቻ ነው፤ ሌላ ምን ለብሶ ይተኛል? ወደ እኔ ሲጮኽ እኔ እሰማለሁ፤ እኔ ርኅሩኅ ነኝና። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 ብርድ የሚከላከልበት ሌላ ምንም ልብስ ስለሌለው ምን ለብሶ ሊያድር ይችላል? እኔ መሐሪ ስለ ሆንኩ እርሱ ወደ እኔ ቢጮኽ እሰማዋለሁ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 ልብሱ ነውና፥ ዕርቃኑንም የሚሸፍንበት ይህ ብቻ ነውና፤ የሚተኛበትም ሌላ የለውምና፤ ወደ እኔም ቢጮኽ ፈጥኜ እሰማዋለሁ፤ መሓሪ ነኝና። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 ሥጋውን የሚከድንበት እርሱ ብቻ ነውና፤ የሚተኛበትም ሌላ የለውምና፤ ወደ እኔም ቢጮኽ መሐሪ ነኝና እሰማዋለሁ። See the chapter |