ዘፀአት 21:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)29 ነገር ግን በሬው አስቀድሞ ተዋጊ ቢሆን፥ ለባለቤቱ አስጠንቅቀውት ባይጠብቀውና ወንድን ወይም ሴትን ቢገድል፥ በሬው ይወገር፥ ባለቤቱ ደግሞ ይገደል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም29 ሆኖም በሬው የመውጋት ዐመል ያለበት ሆኖ ለባለቤቱም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ሳለ በበረት ሳያስቀረው ቀርቶ አንድን ወንድ ወይም ሴት ቢገድል፣ በሬው በድንጋይ ይወገር፤ ባለቤቱም እንዲሁ ተወግሮ ይሙት። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም29 በሬው የተዋጊነት ልማድ ያለው ቢሆንና ባለቤቱም ቀደም ሲል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት በበረት ሳይዘው ቀርቶ ቢሆን ግን በሬው ሰው በሚወጋበት ጊዜ በድንጋይ ተወግሮ ይሙት፤ ባለ ንብረቱም በሞት ይቀጣ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)29 በሬው ግን ከትናንትና ከትናንት ወዲያ ተዋጊ ቢሆን፥ ሰዎችም ለባለቤቱ ቢመሰክሩለት ባያስወግደውም፥ ወንድን ወይም ሴትን ቢገድል፥ በሬው ይወገር፤ ባለቤቱ ደግሞ ይገደል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)29 በሬው ግን አስቀድሞ ተዋጊ ቢሆን፥ ሰዎችም ለባለቤቱ ቢመሰክሩለት ባይጠብቀውም፥ ወንድንም ወይም ሴትን ቢገድል፥ በሬው ይወገር፥ ባለቤቱ ደግሞ ይገደል። See the chapter |