ዘፀአት 21:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ተነሥቶም በምርኩዝ ወደ ውጭ ቢወጣ፥ ሥራ ስላስፈታው ገንዘብ ከመክፈልና፥ እስኪፈወስም ድረስ ከማሳከም በቀር የመታው ሰው ከወንጀል ነጻ ነው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 በትሩንም ይዞ ደጅ ለደጅ የሚል ቢሆን፣ በዱላ የመታው ሰው አይጠየቅበትም፤ ሆኖም ለተጐጂው ሰው ለባከነበት ጊዜ ገንዘብ ይክፈል፤ ፈጽሞ እስኪድን ክትትል ያድርግለት። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 በኋላም ተነሥቶ በትር እየተመረኰዘ መራመድ ቢቀጥል፤ ስለ ባከነበት ጊዜ የመታው ሰው ካሣ ይክፈለው፤ በደንብ እስከሚድንም ድረስ ተገቢውን እንክብካቤ ያድርግለት። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ተነሥቶም በምርኩዝ ወደ ሜዳ ቢወጣ፥ የመታው ንጹሕ ነው፤ ነገር ግን ተግባሩን ስላስፈታው ገንዘብ ይክፈለው፤ ለባለ መድኀኒትም ይክፈልለት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ተነሥቶም በምርኩዝ ወደ ሜዳ ቢወጣ፥ የመታው ንጹሕ ነው፤ ነገር ግን ተግባሩን ስላስፈታው ገንዘብ ይከፍለው ዘንድ፥ ያስፈውሰውም ዘንድ ግዴታ አለበት። See the chapter |