Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፀአት 21:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 አባቱን ወይም እናቱን የሚያዋርድ ፈጽሞ ይሙት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ይገደል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 “አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ በሞት ይቀጣ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 “ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አን​ዱን የሰ​ረቀ ወይም ግፍ የፈ​ጸ​መ​በት፥ ወይም አሳ​ልፎ ቢሰ​ጠው፥ ወይም በእ​ርሱ ዘንድ ቢገኝ፥ እርሱ ይገ​ደል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ፈጽሞ ይገደል።

See the chapter Copy




ዘፀአት 21:17
11 Cross References  

አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ፥ በጽቅድቅ ጨለማ መብራቱ ይጠፋል።


“‘አባቱን ወይም እናቱን የሚያቃልል የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።


አባቱን የሚረግም፥ እናቱንም የማያመሰግን ትውልድ አለ።


በአባትዋ የምታላግጥን የእናትዋንም ትእዛዝ የምትንቅን ዐይን የሸለቆ ቁራዎች ይጐጠጉጡአታል፥ አሞራዎችም ይበሉአታል።


“ሰዎች ቢጣሉ፥ አንዱም ሌላውን በድንጋይ ወይም በቡጢ ቢመታው፥ ባይሞት ነገር ግን በአልጋ ላይ ቢውል፥


“ጌታ አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም፥ አባትህንና እናትህን አክብር።


“አንድ ሰው፥ የአባቱን ወይም የእናቱን ትእዛዝ የማይሰማ፥ ቢቀጡትም የማይታረም እልከኛና ዓመፀኛ ልጅ ቢኖረው፥


ከዚያም በኋላ የከተማዪቱ ሰዎች ሁሉ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩት፤ ክፉውንም ከመካከልህ አስወግድ፤ እስራኤልም ሁሉ ይህን ሰምቶ ይፈራል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements