ዘፀአት 2:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 በነዚያም ቀኖች፥ ሙሴ ባደገ ጊዜ ወደ ወንድሞቹ ወጣ፥ የሥራቸውንም መከራ ተመለከተ፤ የግብጽም ሰው ከወንድሞቹ አንድ የሆነውን ዕብራዊ ሰው ሲመታ አየ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ሙሴ ካደገ በኋላ አንድ ቀን ወገኖቹ ወደሚገኙበት ስፍራ ወጣ፤ በዚያም ተገድደው ከባድ ሥራ ሲሠሩ ተመለከተ፤ ዕብራዊ ወገኑንም አንድ ግብጻዊ ሲደበድበው አየ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ሙሴ ባደገ ጊዜ ወገኖቹን ለመጐብኘት ሄደ፤ ከባድ ሥራ መሥራታቸውን ተመለከተ፤ እንዲያውም አንድ ግብጻዊ ከወገኖቹ አንዱ የሆነውን ዕብራዊ ሲደበድብ አየ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ከብዙ ቀን በኋላ እንዲህ ሆነ፤ ሙሴ አደገ፤ ወደ ወንድሞቹም ወጣ፤ መከራቸውንም ተመለከተ፤ የግብፅም ሰው ከወንድሞቹ ከእስራኤል ልጆች አንዱን ዕብራዊ ሰው ሲመታ አየ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 በዚያም ወራት እንዲህ ሆነ፤ ሙሴ ጎበዝ በሆነ ጊዜ ወደ ወንድሞቹ ወጣ፤ የሥራቸውንም መከራ ተመለከተ፤ የግብፅም ሰው የወንድሞቹን የዕብራውያንን ሰው ሲመታ አየ። See the chapter |