Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፀአት 19:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 የቀንደ መለከቱ ድምፅ እጅግ በበረታና በጸና ጊዜ ሙሴ ተናገረ እግዚአብሔርም በድምፅ መለሰለት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 የመለከቱም ድምፅ እያየለ መጣ። ከዚያም ሙሴ ተናገረ፤ እግዚአብሔርም በድምፅ መለሰለት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 የእምቢልታውም ብርቱ ድምፅ እያከታተለ ማስተጋባት ቀጠለ፤ ሙሴ ሲናገር እግዚአብሔር በነጐድጓድ ይመልስለት ነበር፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የቀ​ንደ መለ​ከ​ቱም ድምፅ እጅግ እየ​ፈ​ጠነ በር​ትቶ ይሰማ ነበር። ሙሴም ተና​ገረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በድ​ምፅ መለ​ሰ​ለት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የቀንደ መለከቱም ድምፅ እጅግ በበረታና በጸና ጊዜ ሙሴ ተናገረ እግዚአብሔርም በድምፅ መለሰለት።

See the chapter Copy




ዘፀአት 19:19
9 Cross References  

ጫንቃውን ከሸክም፥ እጆቹንም በቅርጫት ከመገዛት አራቅሁ።


እንዲህም ሆነ በሦስተኛው ቀን ማለዳ ነጎድጓድ፥ መብረቅና ከባድ ደመና እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምጽ በተራራው ላይ ሆነ፤ በሰፈሩ የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ።


ሙሴም “እጅግ እፈራለሁ፤ እንቀጠቀጥማለሁ፤” እስኪል ድረስ የሚታየው ነገር እጅግ የሚያስፈራ ነበር፤


በሲና ተራራ ላይ ወረድህ፥ ከሰማይም ተናገርሃቸው፤ ቅን ፍርዶችን፥ ታማኝ ሕጎችን፥ መልካም ሥርዓቶችና ትእዛዞችን ሰጠሃቸው።


የማንም እጅ አይንካው፤ የሚነካው ግን በድንጋይ ይወገራል፥ ወይም በፍላጻ ይወጋል፤ እንስሳም ቢሆን፥ ሰውም ቢሆን አይድንም።’ ሳያቋርጥ የመለከት ድምፅ ሲነፋ በዚያን ጊዜ ወደ ተራራው ይውጡ።”


ወደ መለከት ድምፅ፥ ወይም ቃልን ወደሚያሰማ ድምጽ አልመጣችሁም። ያን ነገር የሰሙት ሁሉ ሌላ ቃል እንዳይጨመርባቸው እስኪለምኑ አደረሳቸው፤


ያስተምራችሁ ዘንድ ከሰማይ ድምፁን አሰማችሁ፥ በምድርም ላይ ታላቁን እሳቱን አሳያችሁ፥ ከእሳቱም መካከል የእርሱን ድምፅ ሰማችሁ።።


እኔ በምሳሌ ሳይሆን እፊት ለፊት ከእርሱ ጋር በግልጥ እነጋገራለሁ፤ የጌታንም ሀልዎተ-ቅርፅ ይመለከታል፤ ታዲያ፥ በባርያዬ በሙሴ ላይ ለመናገር ለምን አልፈራችሁም?”


“እነዚህን ቃሎች ጌታ በተራራው ላይ ለጉባኤአችሁ ሁሉ በእሳትና በደመና፥ በድቅድቅ ጨለማው ውስጥ ሆኖ፥ በታላቅ ድምፅ ተናገረ፥ ምንም ምን አልጨመረም። በሁለቱም የድንጋይ ጽላቶች ላይ ጻፋቸው፥ ለእኔም ሰጠኝ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements