ዘፀአት 17:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 እርሱም የዚያን ስፍራ ስም ማሳህና መሪባ ብሎ ጠራው፥ ይህም ስለ እስራኤል ልጆች ጥልና “ጌታ በመካከላችን ነው ወይስ አይደለም?” በማለት ጌታን ስለተፈታተኑት ነው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ስፍራውንም ማሳህና መሪባ ብሎ ጠራው፤ እስራኤላውያን ጠብ ፈጥረው፣ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው ወይስ አይደለም” በማለት እግዚአብሔርን ተፈታትነዋልና። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 እስራኤላውያን “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ወይስ አይደለም?” በማለት በማጒረምረማቸውና እግዚአብሔርን በመፈታተናቸው ያ ስፍራ ማሳህና እና መሪባ ተብሎ ተጠራ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ስለ እስራኤልም ልጆች ክርክር፥ “እግዚአብሔር በመካከላችን ነውን? ወይስ አይደለም?” ሲሉ እግዚአብሔርን ስለ ተፈታተኑት የዚያን ስፍራ ስም “መንሱት” ደግሞም “ጋእዝ” ብሎ ጠራው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ስለ እስራኤልም ልጆች ክርክር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን ነውን ወይስ አይደለም? ሲሉ እግዚአብሔርን ስለተፈታተኑት የዚያን ስፍራ ስም ማሳህ፥ ደግሞም መሪባ ብሎ ጠራው። See the chapter |