ዘፀአት 16:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)33 ሙሴም አሮንን አለው፦ “አንድ ማድጋ ወስደህ ዖሜር ሙሉ መና አኑርበት፥ በትውልዳችሁም ተጠበቆ እንዲኖር በጌታ ፊት አስቀምጠው።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም33 ስለዚህ ሙሴ አሮንን፣ “አንድ ማሰሮ ወስደህ አንድ ጎሞር መና አስቀምጥበት፤ ለሚመጡት ትውልዶች እንዲቈይም በእግዚአብሔር ፊት አስቀምጠው” አለው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም33 ሙሴም አሮንን “አንድ የሸክላ ዕቃ ወስደህ አንድ ኪሎ ተኩል በሚይዝ መስፈሪያ መና አኑርበት፤ ለመጪውም ትውልድ በእግዚአብሔር ፊት ተጠብቆ እንዲኖር አድርግ” አለው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)33 ሙሴም አሮንን፥ “አንድ የወርቅ መሶብ ወስደህ ጎሞር ሙሉ መና አግባበት፤ ለልጅ ልጃችሁም ይጠበቅ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት አኑረው” አለው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)33 ሙሴም እሮንን፦ አንድ ማድጋ ወስደህ ጎሞር ሙሉ መና አግባበት፥ ለልጅ ልጃችሁም ይጠበቅ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት አኑረው አለው። See the chapter |