Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፀአት 16:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 የእስራኤልም ቤት ስሙን መና ብለው ጠሩት፤ እርሱም እንደ ድንብላል ፍሬ ነጭ ነው፤ ጣዕሙም እንደ ማር ቂጣ ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 የእስራኤልም ሕዝብ ምግቡን መና አሉት፤ እርሱም እንደ ድንብላል ዘር ነጭ፣ ጣሙም ከማር እንደ ተጋገረ ቂጣ ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 እስራኤላውያን ያን ምግብ “መና” ብለው ጠሩት፤ እርሱም እንደ ድንብላል ፍሬ ነጭ የሆነ ነበር፤ ጣዕሙም ከማር ጋር እንደ ተጋገረ ቂጣ ነበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ስሙን መና ብለው ጠሩት፤ እር​ሱም እንደ ድን​ብ​ላል ዘር ነጭ ነው፤ ጣዕ​ሙም እንደ ማር እን​ጀራ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 እርሱም እንደ ድንብላል ዘር ነጭ ነው፤ ጣዕሙም እንደ ማር ቂጣ ነው።

See the chapter Copy




ዘፀአት 16:31
8 Cross References  

በዱር እንዳለ እንኮይ፥ እንዲሁ ውዴ በጐልማሶች መካከል ነው። ከጥላው በታች እጅግ ወድጄ ተቀመጥሁ፥ ፍሬውም ለጉሮሮዬ ጣፋጭ ነው።


የእስራኤልም ልጆች ባዩት ጊዜ ያ ምን እንደሆነ አላወቁምና ሁሉም ሰው ወንድሙን፦ “ይህ ምንድነው?” በማለት ተጠያየቁ። ሙሴም፦ “እንድትበሉት ጌታ የሰጣችሁ ምግብ ነው።”


ጤዛውም ከተነነ በኋላ፥ በመሬት ላይ ስስ የሆነ ቅርፊት የሚመስል ደቃቅ ነገር በምድረ በዳ መሬት ላይ ታየ።


ሕዝቡም በሰባተኛው ቀን ዐረፈ።


ሙሴም፦ “ጌታ ያዘዘው ነገር ይህ ነው፦ ከግብጽ ምድር ባወጣኋችሁ ጊዜ በምድረ በዳ ያበላኋችሁን ምግብ እንዲያዩ ከእርሱ አንድ ዖሜር ሙሉ በትውልዳችሁ ሁሉ ይጠበቅ” አለ።


ሰው የሚኖረው በእንጀራ ብቻ ሳይሆን ከጌታ አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት እንዲኖር ሊያሳውቅህ አስጨነቀህ፥ አስራበህም፥ አንተም ያላወቅኸውን፥ አባቶችህም ያላወቁትን መና አበላህ።


በመጨረሻም መልካም ነገር ሊያደርግልህ፥ ሊፈትንህ ሊያዋርድህም አባቶችህ ያላወቁትን መና በምድረ በዳ ያበላህን፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements