ዘፀአት 13:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ጌታም ወደ ከነዓናውያን፥ ወደ ኬጢያውያን፥ ወደ አሞራውያን፥ ወደ ኤዊያውያን፥ ወደ ኢያቡሳውያንም ለአንተ ሊሰጣት ለአባቶችህ ወደ ማለላቸው፥ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር ባገባህ ጊዜ ይህችን አገልግሎት በዚህ ወር ታገለግላለህ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 እግዚአብሔር ለእናንተ ለመስጠት ሲል ቀድሞ ለአባቶቻችሁ ወደ ማለላቸው ማርና ወተት ወደምታፈስሰው ወደ ከነዓናውያን፣ ኬጢያውያን፣ አሞራውያን፣ ኤዊያውያን፣ ኢያቡሳውያን ምድር በምትገቡበት ጊዜ ይህን በዓል በዚህ ወር ታከብራላችሁ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 የከነዓናውያንን፥ የሒታውያንን፥ የአሞራውያንን፥ የሒዋውያንንና የኢያቡሳውያንን ምድር እንደሚያወርሳችሁ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻችሁ በመሐላ ቃል ኪዳን ገብቶአል፤ በማርና በወተት ወደ በለጸገችው ወደዚያች ለም ምድር በሚያገባችሁ ጊዜ በዓመቱ መጀመሪያ ወር ላይ ይህን በዓል ታከብሩታላችሁ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 እግዚአብሔርም ለእናንተ ይሰጣት ዘንድ ለአባቶቻችሁ ወደማለላቸው፥ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር፥ ወደ ከናኔዎናውያን፥ ወደ ኬጢዎናውያንም፥ ወደ አሞሬዎናውያንም፥ ወደ ኤዌዎናውያን፥ ወደ ኢያቡሴዎናውያንም፥ ወደ ጌርጌሴዎናውያንም፥ ወደ ፌርዜዎናውያንም ምድር በአገባችሁ ጊዜ ይህችን ሥርዐት በዚህ ወር አድርጉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 እግዚአብሔርም ለአንተ ይሰጣት ዘንድ ለአባቶችህ ወደ ማለላቸው፥ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር፥ ወደ ከነዓናውያን ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ኢያቡሳውያንም ምድር ባገባህ ጊዜ ይህችን አምልኮ በዚህ ወር ታደርጋለህ። See the chapter |