Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፀአት 12:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 ከግብጽም ከእነርሱ ጋር ያወጡትን ሊጥ ጋገሩ፥ አልቦካም ነበርና ቂጣ አደረጉት፤ ግብፃውያን በመውጣት ስላስቸኮሉአቸው ይቆዩ ዘንድ አልተቻላቸውም፥ ስንቅም አላሰናዱም ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 ከግብጽ ይዘው ከወጡት ሊጥ ያልቦካ ቂጣ ጋገሩ፤ ሊጡ አልቦካም ነበር፤ ምክንያቱም ከግብጽ በጥድፊያ እንዲወጡ ስለተደረጉ፣ ለራሳቸው ምግብ ለማዘጋጀት ጊዜ አልነበራቸውም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 ከግብጽ በድንገት ተጣድፈው ስለ ወጡ ምግባቸውን ለማዘጋጀትም ሆነ በእርሾ የቦካ እንጀራ ለመጋገር ጊዜ ስላልነበራቸው ከግብጽ ይዘው ካወጡትም ሊጥ ቂጣ ጋገሩ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 ከግ​ብ​ፅም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ያወ​ጡ​ትን ሊጥ ቂጣ እን​ጎቻ አድ​ር​ገው ጋገ​ሩት። አል​ቦ​ካም ነበ​ርና፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ስለ አስ​ወ​ጡ​አ​ቸው ይቈዩ ዘንድ አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ምና፤ ለመ​ን​ገ​ድም ስንቅ አላ​ሰ​ና​ዱም ነበ​ርና።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 ከግብፅም ከእነርሱ ጋር ያወጡትን ሊጥ ጋገሩ፤ አልቦካም ነበርና ቂጣ እንጎቻ አደረጉት፤ ግብፃውያን በመውጣት ስላስቸኮሉአቸው ይቆዩ ዘንድ አልተቻላቸውም፤ ስንቅም አላሰናዱም ነበር።

See the chapter Copy




ዘፀአት 12:39
5 Cross References  

ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በፈርዖንና በግብጽ ላይ ገና አንድ መቅሰፍት አመጣለሁ፥ ከዚያ በኋላ ከዚህ ይለቅቃችኋል፤ ሲለቅቃችሁም ሙሉ በሙሉ ያባርራችኋል።


ጌታም ሙሴን አለው፦ “አሁን ፈርዖንን ምን እንደማደርገው ታያለህ በጸናች እጅ ይለቅቃቸዋል፥ በጸናችም እጅ ከምድሩ አስወጥቶ ይሰድዳቸዋል።”


ሌላ ምሳሌ እንዲህ ሲል ነገራቸው፤ “መንግሥተ ሰማያት አንዲት ሴት ወስዳ ሁሉ እስኪቦካ ድረስ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት ውስጥ የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች።”


ሕዝቡም ሊጡን ሳይቦካ ተሸከሙ፥ ማቡኪያውንም በልብሳቸው ጠቅልለው በትከሻቸው ተሸከሙት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements