Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፀአት 12:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ጌታም ለሕዝቡ በግብፃውያን ፊት ሞገስን ሰጣቸው እነርሱም የፈለጉትን ሰጡአቸው። እነርሱም ግብጽን በዘበዙ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 እግዚአብሔር በግብጻውያን ፊት ለእስራኤላውያን ሞገስ ስለ ሰጣቸው፣ የጠየቋቸውን ሁሉ ሰጧቸው፤ ስለዚህ የግብጻውያንን ንብረት በዝብዘው ወሰዱ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 እግዚአብሔርም እስራኤላውያን በግብጻውያን ዘንድ ሞገስ እንዲያገኙና የጠየቁትንም ሁሉ ማግኘት እንዲችሉ አደረገ፤ በዚህም ዐይነት እስራኤላውያን የግብጽን ሀብት በዝብዘው ሄዱ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሕ​ዝቡ በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ፊት ሞገ​ስን ሰጠ፤ እነ​ር​ሱም አዋ​ሱ​አ​ቸው። እነ​ር​ሱም ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን በዘ​በ​ዙ​አ​ቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 እግዚአብሔርም ለሕዝቡ በግብፃውያን ፊት የፈለጉትን እንዲሰጡአቸው ሞገስን ሰጠ። እነርሱም ግብፃውያንን በዘበዙ።

See the chapter Copy




ዘፀአት 12:36
11 Cross References  

ከመከራውም ሁሉ አወጣው፤ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖንም ፊት ሞገስንና ጥበብን ሰጠው፤ በግብጽና በቤቱ ሁሉ ላይም ቢትወደድ አድርጎ ሾመው።


ደግሞም በባርነት በሚገዙአቸው ሕዝብ ላይ እኔ እፈርዳለሁ፥ ከዚያም በኋላ በብዙ ከብት ይወጣሉ።


ከወርቅና ከብርም ጋር አወጣቸው፥ በወገናቸውም ውስጥ የተደናቀፈ አልነበረም።


ጌታም ለሕዝቡ በግብፃውያን ፊት ሞገስን ሰጠ። ሙሴም በግብጽ ምድር፥ በፈርዖን አገልጋዮች ፊትና በሕዝቡ ፊት እጅግ ታላቅ ሰው ነበረ።


ይሁን እንጂ ዮሴፍ እዚያ እስር ቤት ባለበት ጊዜ ሁሉ፥ ጌታ ከእርሱ ጋር ነበረ፤ ቸርነቱንም አበዛለት፥ በወህኒ አዛዡም ዘንድ ሞገስን ሰጠው።


እግዚአብሔርም እያመሰገኑ በሕዝብ ሁሉ ፊት ሞገስ ነበራቸው። ጌታም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር።


የሰው አካሄድ ጌታን ደስ ያሰኘው እንደሆነ፥ በእርሱና በጠላቶቹ መካከል ስንኳ ሰላምን ያደርጋል።


ወንዱ ከጎረቤቱ ሴቲቱም ከጎረቤቷ የብር ዕቃና የወርቅ ዕቃ እንዲጠይቁ በሕዝቡ ጆሮ ተናገር።”


በዙሪያቸውም ያሉ ሁሉ በፈቃዳቸው ካቀረቡት መባ ሁሉ በተጨማሪ በእጃቸው፥ በብር ዕቃና በወርቅ፥ በዕቃዎችና በእንስሶችና በውድ ነገሮች አበረታቱአቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements