Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፀአት 12:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 የእስራኤልም ልጆች እንደ ሙሴ ቃል አደረጉ፥ ከግብፃውያንም የብርንና የወርቅን ዕቃ ልብስንም ለመኑ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 እስራኤላውያን ሙሴ እንዳዘዛቸው የብርና የወርቅ ዕቃዎች፣ እንደዚሁም ልብስ እንዲሰጧቸው ግብጻውያኑን ጠየቋቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 እስራኤላውያን ሙሴ እንዳዘዛቸውም አደረጉ፤ ይኸውም የወርቅና የብር ጌጣጌጥ እንዲሁም ልብስ እንዲሰጡአቸው ግብጻውያንን ጠየቁ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሙሴ እን​ዳ​ዘዘ አደ​ረጉ። ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም የብ​ር​ንና የወ​ር​ቅን ዕቃ፥ ልብ​ስ​ንም ተዋሱ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 የእስራኤልም ልጆች ሙሴ እንዳዘዘ አደረጉ፤ ከግብፃውያንም የብርንና የወርቅን ዕቃ ልብስንም ለመኑ።

See the chapter Copy




ዘፀአት 12:35
8 Cross References  

ከወርቅና ከብርም ጋር አወጣቸው፥ በወገናቸውም ውስጥ የተደናቀፈ አልነበረም።


ደግሞም በባርነት በሚገዙአቸው ሕዝብ ላይ እኔ እፈርዳለሁ፥ ከዚያም በኋላ በብዙ ከብት ይወጣሉ።


ሎሌውም የብርና የወርቅ ጌጥ ልብስም አወጣ፥ ለርብቃም ሰጣት፥ የከበረ ስጦታንም ለወንድምዋና ለእናትዋ አቀረበ።


የእስራኤልም ልጆች ሄዱ፥ እንዲሁም አደረጉ፤ ጌታ ሙሴንና አሮንን እንዳዘዘ እንዲሁ አደረጉ።


በዙሪያቸውም ያሉ ሁሉ በፈቃዳቸው ካቀረቡት መባ ሁሉ በተጨማሪ በእጃቸው፥ በብር ዕቃና በወርቅ፥ በዕቃዎችና በእንስሶችና በውድ ነገሮች አበረታቱአቸው።


ለመፈለግ ጊዜ አለው፥ ለማጥፋትም ጊዜ አለው፥ ለመጠበቅ ጊዜ አለው፥ ለመጣልም ጊዜ አለው፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements