ዘፀአት 12:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ለእስራኤል ልጆች ማህበር ሁሉ እንዲህ ብላችሁ ንገሩ። በዚህ ወር በአሥረኛው ቀን ሰው ሁሉ ለአባቱ ቤት አንድ ጠቦት፥ ለአንድ ቤትም አንድ ጠቦት ይውሰድ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ለመላው የእስራኤል ሕዝብ ይህን ንገሩ፤ ይህ ወር በገባ በዐሥረኛው ቀን እያንዳንዱ ሰው አንዳንድ ጠቦት ለቤተ ሰቡ፣ አንዳንድ ጠቦት ለአባቱ ቤት ያዘጋጅ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ለመላው የእስራኤል ሕዝብ ይህን ሥርዓት አስተምሩ፤ ይህ ወር በገባ በዐሥረኛው ቀን እያንዳንዱ ሰው በቤተሰቡ ደረጃ አንድ ጠቦት ይምረጥ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ተናገሩ፤ በሉአቸውም፦ በዚህ ወር በዐሥረኛው ቀን ሰው ሁሉ ለአባቱ ቤተ ሰቦች ቤቶች አንድ አንድ ጠቦት፥ እያንዳንዱ ሰውም ለራሱ ቤተ ሰብእ አንድ ጠቦት ይውሰድ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ተናገሩ፥ በሉአቸውም፥ በዚህ ወር በአሥረኛው ቀን ሰው ሁሉ ለአባቱ ቤት አንድ ጠቦት፥ ለአንድ ቤትም አንድ ጠቦት ይውሰድ። See the chapter |