Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፀአት 12:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ጌታ ግብጽን ሊመታ ያልፋል፤ ደሙንም በጉበኖቹና በሁለቱ መቃኖች ላይ ያያል፥ ጌታም በበሩ ያልፋል፥ አጥፊውም ሊመታችሁ ወደ ቤታችሁ እንዲገባ አይፈቅድም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እግዚአብሔር ግብጻውያንን ለመቅሠፍ በምድሪቱ ላይ በሚያልፍበት ጊዜ በጕበኑና በመቃኑ ላይ ያለውን ደም ሲያይ ያን ደጃፍ ዐልፎ ይሄዳል፤ ቀሣፊውም ወደ ቤታችሁ ገብቶ እንዳይገድላችሁ ይከለክለዋል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 እግዚአብሔር ግብጻውያንን በሞት ለመቅጣት በግብጽ ምድር ያልፋል፤ በጉበንና በመቃኖቹ ላይ ያለውንም ደም በሚያይበት ጊዜ አልፎ ይሄዳል፤ የሞት መልአክም ወደየቤታችሁ ገብቶ እናንተን እንዳይገድል ያደርጋል፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን ይመታ ዘንድ ያል​ፋ​ልና፤ ደሙ​ንም በጉ​በ​ኑና በሁ​ለቱ መቃ​ኖች ላይ በአየ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሩን ያል​ፋል፤ አጥ​ፊ​ውም ይመ​ታ​ችሁ ዘንድ ወደ ቤታ​ችሁ እን​ዲ​ገባ አይ​ተ​ወ​ውም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እግዚአብሔር ግብፃውያንን ይመታ ዘንድ ያልፋልና፤ ደሙንም በጉበኑና በሁለቱ መቃኖች ላይ ባየ ጊዜ እግዚአብሔር በደጁ ላይ ያልፋል፤ አጥፊውም ይመታችሁ ዘንድ ወደ ቤታችሁ እንዲገባ አይተውም።

See the chapter Copy




ዘፀአት 12:23
14 Cross References  

የእግዚአብሔርም ማኅተም በግምባራቸው ከሌለባቸው ሰዎች በቀር በምድር ያለውን ሣር ቢሆንም ወይም ማናቸውንም የለመለመ ነገር ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጐዱ ተነገራቸው።


“የአምላካችንን ባርያዎች ግምባራቸውን እስክናትማቸው ድረስ ምድርንም ሆነ ባሕርን ወይም ዛፎችን አትጉዱ፤” አላቸው።


የበኩር ልጆችን የሚያጠፋው እንዳይነካቸው ፋሲካን የጠበቀውና ደምን መርጨትን ያደረገው በእምነት ነበር።


ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንዳጉረመረሙና በሚያጠፋውም እንደ ጠፉ አታጉረምርሙ።


ሽማግሌ፥ ወጣት፥ ድንግል፥ ሕፃናትንና ሴቶችን ግደሉ፥ ነገር ግን ምልክቱ ወዳለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ፥ በመቅደሴም ጀምሩ። በቤቱ ፊት ለፊት ከነበሩት ሽማግሌዎች ጀመሩ።


የጌታም መልአክ ወጣ፥ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉ በድኖች ነበሩ።


የጌታ መልአክ ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት እጁን በዘረጋ ጊዜ፥ ጌታ ስለ ክፉው ነገር አዘነ፤ ሕዝቡን የሚቀሥፈውንም መልአክ “ይበቃል! እጅህን መልስ” አለው። በዚያን ጊዜ የጌታ መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።


የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።


ጌታም እንዲህ አለው፦ በከተማይቱ መካከል፥ በኢየሩሳሌም መካከል እለፍ፥ በመካከልዋም ስለ ተሠራው ርኩሰት ሁሉ በሚተክዙና በሚያለቅሱ ሰዎች ግምባር ላይ ምልክትን አድርግ።


ሙሴም እንዲህ አለ፦ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ በእኩለ ሌሊት እኔ በግብጽ መካከል እወጣለሁ፤


ከደሙም ጥቂት ወስደው በሚበሉበት ቤት ሁለቱን መቃንና ጉበኑን ይቀቡት።


ሕዝቤ ሆይ፥ ና ወደ ቤትህም ግባ፥ ደጅህን ከጀርባህ ዝጋ፤ ቁጣ እስኪያልፍ ድረስ ጥቂት ጊዜ ተሸሸግ።


በሲኦል ውስጥ ምነው በሰወርኸኝ ኖሮ! ቁጣህ እስኪያልፍ ድረስ በሸሸግኸኝ ኖሮ! ቀጠሮም አድርገህ ምነው ባሰብኸኝ ኖሮ!


Follow us:

Advertisements


Advertisements