ዘፀአት 11:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 በግብጽም ምድር ያለ በኩር ሁሉ፥ በዙፋኑ ከሚቀመጠው ከፈርዖን በኩር ጀምሮ በወፍጮ እግር እስካለችው እስከ ባርያይቱ በኩር ድረስ፥ የከብቱም በኩር ሁሉ ይሞታል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ከፈርዖን ልጅ አንሥቶ የወፍጮ መጅ ገፊ እስከ ሆነችው እስከ ባሪያዪቱ ልጅ ድረስ በግብጽ ምድር በኵር ሆኖ የተወለደ ወንድ ልጅ ሁሉ ይሞታል፤ እንዲሁም የቀንድ ከብቱ በኵር በሙሉ ያልቃል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 የዙፋኑ ወራሽ ከሆነው ከንጉሡ ልጅ ጀምሮ እህል በመፍጨት ከምታገለግል ድኻ ሴት እስከ ተወለደው ልጅ ድረስ በግብጽ ምድር በኲር የሆነ ወንድ ልጅ ሁሉ ይሞታል፤ እንዲሁም የእንስሶች በኲር ሁሉ ይሞታል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 በግብፅም ሀገር ያለ በኵር ሁሉ፥ በዙፋኑ ከሚቀመጠው ከፈርዖን በኵር ጀምሮ በወፍጮ እግር እስካለችው እስከ አገልጋዪቱ በኵር ድረስ፥ የከብቱም በኵር ሁሉ ይሞታል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 በግብፅም አገር ያለ በኵር ሁሉ፥ በዙፋኑ ከሚቀመጠው ከፈርዖን በኵር ጀምሮ በወፍጮ እግር እስካለችው እስከ ባሪያይቱ በኵር ድረስ፥ የከብቱም በኵር ሁሉ ይሞታል። See the chapter |