ዘፀአት 11:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በፈርዖንና በግብጽ ላይ ገና አንድ መቅሰፍት አመጣለሁ፥ ከዚያ በኋላ ከዚህ ይለቅቃችኋል፤ ሲለቅቃችሁም ሙሉ በሙሉ ያባርራችኋል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “በፈርዖንና በግብጽ ላይ አንድ ሌላ መቅሠፍት አወርድባቸዋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ፈርዖን ይለቅቃችኋል፤ ሲለቅቃችሁም አንዳችሁን ሳያስቀር ያስወጣችኋል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “በግብጽ ንጉሥና በሕዝቡም ሁሉ ላይ ሌላ መቅሠፍት እልካለሁ፤ ከዚያም በኋላ ከዚህች ምድር እንድትወጡ ይለቃችኋል፤ እንዲያውም አንድ ሳይቀር ሁላችሁንም ያባርራችኋል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “በፈርዖንና በግብፅ ላይ ገና አንዲት መቅሠፍት አመጣለሁ፤ ከዚያም በኋላ ከዚያ ይለቅቃችኋል፤ ሲለቅቃችሁም ከመነሻ ገንዘብ ጋር ይሰድዳችኋል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ “በፈርዖንና በግብፅ ላይ ገና አንዲት መቅሰፍት አመጣለሁ፤ ከዚያ ወዲያም ይለቅቃችኋል፤ ሲለቅቃችሁም አባርሮ ይሰድዳችኋል። See the chapter |