Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘፀአት 10:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ሙሴም፦ “ወጣቶቻችን፥ ሽማግሌዎቻችን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን፥ በጎቻችንና ከብቶቻችን ከእኛ ጋር ይሄዳሉ የጌታን በዓል እናደርጋለንና” አለ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ሙሴም፣ “ለእግዚአብሔር በዓል ልናከብር ስለ ሆነ ወጣቶቻችንንና ሽማግሌዎቻችንን፣ ወንድና ሴት ልጆቻችንን፣ የበግና የፍየል መንጋዎቻችንን እንዲሁም የቀንድ ከብቶቻችንን ይዘን እንሄዳለን” አለ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ሙሴም “ሕፃን ልጆቻችንና ሽማግሌዎቻችን ሳይቀሩ ሁላችንም እንሄዳለን፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንን፥ በጎቻችንንና ፍየሎቻችንን፥ የቀንድ ከብቶቻችንንም ሁሉ እንወስዳለን፤ በምንሄድበት ስፍራ ለእግዚአብሔር በዓል እናደርጋለን” ሲል መለሰ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ሙሴም አለው፥ “እኛ ከታ​ና​ና​ሾ​ቻ​ች​ንና ከሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ችን፥ ከወ​ን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ችን ጋር እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በጎ​ቻ​ች​ን​ንና ላሞ​ቻ​ች​ን​ንም እን​ወ​ስ​ዳ​ለን። የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል ነውና።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ሙሴም፦ “እኛ እንሄዳለን፤ የእግዚአብሔርም በዓል ሆኖልናልና ታናናሾቻችንና ሽማግሌዎቻችን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንም፥ በጎቻችንና ከብቶቻችንም ከእኛ ጋር ይሄዳሉ፤” አለ።

See the chapter Copy




ዘፀአት 10:9
19 Cross References  

ከዚህም በኋላ ሙሴና አሮን ሄደው ፈርዖንን እንዲህ አሉት፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በምድረ በዳ በዓል እንዲያደርግልኝ ሕዝቤን ልቀቅ።’”


እነርሱም ቃልህን ይሰማሉ፤ አንተና የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ግብጽ ንጉሥ ትሄዳላችሁ፦ ‘የዕብራውያን አምላክ ጌታ ተገለጠልን፤ ስለዚህ ለአምላካችን ለጌታ እንድንሠዋ የሦስት ቀን መንገድ በምድረ በዳ እንሂድ’ ትሉታላችሁ።


እናንተም አባቶች ሆይ! ልጆቻችሁን በጌታ ምክርና በተግሣጽ አሳድጉአቸው እንጂ አታስቈጡአቸው።


የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ፥ ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ፥


ከሀብትህ አስበልጠህ ጌታን አክብር፥ ከፍሬህም ሁሉ በኵራት ይልቅ፥


ጌታንም ማገልገል ክፉ መስሎ ቢታያችሁ፥ አባቶቻችሁ በወንዝ ማዶ ሳሉ ያገለገሉአቸውን አማልክት ወይም በምድራቸው የተቀመጣችሁባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታገለግሉ እንደሆነ፥ የምታገለግሉትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን ጌታን እናገለግላለን።”


በሰባተኛውም ወር በዓሥራ አምስተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት፥ ሰባት ቀንም ለጌታ በዓል አድርጋችሁ ታከብራላችሁ።


ሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ ትበላለህ፥ በሰባተኛውም ቀን ለጌታ በዓል ይሆናል።


እነርሱም፦ “የዕብራውያን አምላክ ተገናኘን፤ የሦስት ቀን መንገድ በምድረ በዳ እንድንሄድ፥ ለጌታ ለአምላካችን እንድንሠዋ እንለምንሃለን ካልሆነ ተላላፊ በሽታ ወይም ሰይፍ እንዳይጥልብን” አሉት።


የዮሴፍም ቤተሰቦች ሁሉ፥ ወንድሞቹም የአባቱም ቤተሰቦች ወጡ፥ ልጆቻቸውንና በጎቻቸውን ከብቶቻቸውን ብቻ በጌሤም ተዉ።


እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ጌታ ከእናንተ ጋር ይሁን እናንተንና ልጆቻችሁን እለቅቃለሁ፥ ነገር ግን ክፉ ነገር በፊታችሁ እንደሚሆን ተመልከቱ።


ከብቶቻችን ከእኛ ጋር ይሄዳሉ አንድ ሰኮናም አይቀርም፥ ጌታ አምላካችንን ለማገልገል ከእነርሱ እንወስዳለንና፤ ጌታን የምናገለግለው በምን እንደሆነ እዚያ እስክንደርስ አናውቅም።”


እንዳላችሁትም መንጎቻችሁንና ከብቶቻችሁን ውሰዱ፥ ሂዱም፥ እኔንም ደግሞ ባርኩኝ።”


የእስራኤልም ልጆች ከራዓምሴስ ወደ ሱኮት በእግር ተጓዙ፤ ከሕፃናቱም ሌላ ስድስት መቶ ሺህ ሰው የሚያህሉ ነበሩ።


ደግሞም ሌላ ብዙ ድብልቅ ሕዝብ መንጎችና ላሞችም እጅግ ብዙም ከብቶች ከእነርሱ ጋር ወጡ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements