Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መክብብ 5:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እግዚአብሔር በልቡ ደስታን እስካኖረ ድረስ፥ እርሱ የሕይወቱን ዘመን እጅግም አያስብም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 አምላክ ለሰው ባለጠግነትና ሀብት መስጠቱ፣ እንዲደሰትበትም ማስቻሉ፣ ዕጣውን እንዲቀበልና በሥራውም እንዲደሰት ማድረጉ፣ ይህ የአምላክ ስጦታ ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እግዚአብሔር ለሰው ሀብትና ብልጽግናን መስጠቱ የደከመበትን ድርሻ አግኝቶ በመብላትና በመጠጣት ደስ እንዲለው ፈቅዶለት ነው፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ሁሉ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ት​ንና ሀብ​ትን መስ​ጠቱ፥ ከእ​ር​ስ​ዋም ይበ​ላና ዕድል ፈን​ታ​ውን ይወ​ስድ ዘንድ፥ በድ​ካ​ሙም ደስ ይለው ዘንድ ማሠ​ል​ጠኑ ይህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስጦታ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ ባለጠግነትንና ሀብትን መስጠቱ፥ ከእርስዋም ይበላና እድል ፈንታውን ይወስድ ዘንድ በድካሙም ደስ ይለው ዘንድ ማሠልጠኑ፥ ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።

See the chapter Copy




መክብብ 5:19
6 Cross References  

ባለጸጋ እንድትሆን ኃይልና ብርታት የሰጠህ ጌታ አምላክህ መሆኑን አስታውስ፤ ይህም ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ ነው።


ደግሞም የእግዚአብሔር ስጦታ ሰው ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ በድካሙም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ ነው።


እግዚአብሔር ለሰው ሀብትን፥ ንብረትንና ክብርን ሰጠው፥ ከወደደውም ነገር ሁሉ ለነፍሱ አልጐደለውም፤ ነገር ግን ሌላ ሰው ይበላዋል እንጂ ከእርሱ ይበላ ዘንድ እግዚአብሔር ሥልጣን አልሰጠውም፤ ይህም ከንቱና ክፉ ደዌ ነው።


ጥበብንና እውቀትን ሰጥቼሃለሁ፤ ከአንተ በፊትም ከነበሩት ከአንተም በኋላ ከሚነሡት ነገሥታት አንድም እንኳ የሚመስልህ እንዳይኖር አድርጌ ባለጠግነትንና ሀብትን ክብርንም እሰጥሃለሁ።”


ከዚህም በላይ አንተ ያልጠየቅከውንም ሁሉ ጨምሬ እሰጥሃለሁ፤ ይኸውም በዘመንህ ማንኛውም ሌላ ንጉሥ ያላገኘውን ብልጽግናና ክብር አበዛልሃለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements