መክብብ 5:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ ሀብትና ንብረት መስጠቱ፥ ከእርሷም ይበላና እድል ፈንታውን ይወስድ ዘንድ በድካሙም ደስ ይለው ዘንድ ሥልጣን መስጠቱ ነው፥ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 የሰው ዕጣው ይህ ስለ ሆነ፣ አምላክ በሰጠው በጥቂት ዘመኑ ከፀሓይ በታች በሚደክምበት ነገር ርካታን ያገኝ ዘንድ፣ መብላቱና መጠጣቱም መልካምና ተገቢ መሆኑን ተገነዘብሁ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 እንግዲህ እኔ የተመለከትኩት የተሻለ ነገር ቢኖር ሰው በዚህ ዓለም ሳለ እግዚአብሔር በሰጠው አጭር ዕድሜ የደከመበትን ሁሉ በመብላትና በመጠጣት መደሰቱ ነው፤ የሰው ዕድል ፈንታም ይኸው ብቻ ነው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 እነሆ፥ እኔ ያየሁት መልካምና የተዋበ ነገር፦ ሰው እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ፥ ከፀሐይ በታችም በሚደክምበት ድካም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ ነው፤ ይህ ዕድል ፈንታው ነውና። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 እነሆ፥ እኔ ያየሁት መልካምና የተዋበ ነገር ሰው እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ፥ ከፀሐይ በታችም በሚደክምበት ድካም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ ነው፥ ይህ እድል ፈንታው ነውና። See the chapter |