መክብብ 5:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ከፀሐይ በታች የሚያሳዝን ክፉ ነገር አየሁ፥ ራስን ለመጉዳት በባለቤቱ ዘንድ የተቀመጠ ሀብት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 ጥቂትም ይሁን ብዙ ቢበላ፣ የሠራተኛ እንቅልፍ ጣፋጭ ነው፤ የሀብታም ሰው ብልጽግና ግን እንቅልፍ ይነሣዋል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 የጉልበት ሥራ የሚሠራ ሰው ብዙም ሆነ ጥቂት ቢመገብ የሰላም እንቅልፍ አግኝቶ ያድራል፤ የባለ ጸጋ ሰው የሀብት ብዛት ግን ሀብቱ እንቅልፍ ይነሣዋል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 ብዙ ወይም ጥቂት ቢበላ የአገልጋይ እንቅልፉ ጣፋጭ ነው፤ ብልጽግናን ያበዛ ሰውን ግን ይተኛ ዘንድ የሚተወው የለም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 እጅግ ወይም ጥቂት ቢበላ የሠራተኛ እንቅልፍ ጣፋጭ ነው የባለጠጋ ጥጋብ ግን እንቅልፍን ይከለክለዋል። See the chapter |