መክብብ 4:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ከእርሱ በፊት የተገዙለት ሕዝብ ሁሉ ስፍር ቍጥር አልነበራቸውም፥ በኋላ የሚመጡት ግን በእርሱ ደስ አይላቸውም። ይህም ደግሞ ከንቱ፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 በፊቱ የነበረው ሕዝብ ሁሉ ቍጥር ስፍር አልነበረውም፤ ከርሱ በኋላ የመጡት ግን በተተኪው አልተደሰቱም። ይህም ደግሞ ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 ንጉሥ ሆኖ በሚያስተዳድርበት ጊዜ የሚገዛለት ሕዝብ ብዛት እጅግ ብዙ ነው፤ ከዙፋኑ ላይ በታጣ ጊዜ ግን ስላደረገው ነገር ሁሉ የሚያመሰግነው አንድ ሰው እንኳ አይገኝለትም፤ ይህም ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር የሚቈጠር ከንቱ ነገር ነው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ከእርሱ በፊት የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ቍጥር የላቸውም፤ በኋላ የሚመጡት ግን በእርሱ ደስ አይላቸውም። ይህ ደግሞ ከንቱ ነው፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ከእርሱ በፊት የተገዙለት ሕዝብ ሁሉ አይቈጠሩም፥ በኋላ የሚመጡት ግን በእርሱ ደስ አይላቸውም። ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው። See the chapter |