Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መክብብ 4:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 አንዱም አንድን ሰው ቢያሸንፍ፥ ሁለቱ ግን ይቋቋሙታል፥ በሦስትም የተገመደ ገመድ በፍጥነት አይበጠስም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 አንድ ሰው ብቸኛውን ቢያጠቃውም፣ ሁለት ከሆኑ ይመክቱታል፤ በሦስት የተገመደ ገመድም ቶሎ አይበጠስም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 አንድ ሰው ብቻውን ሊመልሰው የማይችለውን አደጋ ሁለት ሰዎች ሊቋቋሙት ይችላሉ፤ በሦስት ተሸርቦ የተገመደ ፈትል እንኳ በቀላሉ አይበጠስም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አን​ዱም ሌላ​ውን ቢያ​ሸ​ንፍ ሁለቱ በፊቱ ይቆ​ማሉ፤ በሦ​ስ​ትም የተ​ገ​መደ ገመድ ፈጥኖ አይ​በ​ጠ​ስም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 አንዱም አንዱን ቢያሸንፍ ሁለቱ በፊቱ ይቆማሉ፥ በሦስትም የተገመደ ገመድ ፈጥኖ አይበጠስም።

See the chapter Copy




መክብብ 4:12
8 Cross References  

በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።


ከእርሱ ቀጥሎ የአሆህዊው የዶዶ ልጅ ኤልዔዘር ነበረ፤ እርሱም ለጦርነት አንድ ላይ ተሰብስበው የነበሩትን ፍልስጥኤማውያንን በተገዳደሩ ጊዜ፥ ከዳዊት ጋር ከነበሩት ከሦስቱ ኀያላን ሰዎች አንዱ ነበር። ከዚያም የእስራኤል ሰዎች አፈገፈጉ።


ከሠላሳዎቹ ይልቅ የከበረ ሰው ነበረ፤ ነገር ግን ከሦስቱ እንደ አንዱ አልነበረም። ዳዊትም የክብር ዘበኞቹ አለቃ አድርጎ ሾመው።


ሦስቱም ኀያላን በፍልስጥኤማውያን ሠራዊት መካከል ሰንጥቀው በማለፍ፥ በበሩ አጠገብ ካለችው ከቤተልሔም ጉድጓድ ውሃ ቀድተው ለዳዊት አመጡለት። እርሱ ግን አልጠጣውም፤ ይልቁን በጌታ ፊት አፈሰሰው፤


ሁለቱም በአንድነት ቢተኙ ይሞቃቸዋል፥ አንድ ብቻውን ግን እንዴት ይሞቀዋል?


ድኀና ጠቢብ ወጣት ተግሣጽን መቀበል ካቃተው አላዋቂ ሽማግሌ ንጉሥ ይሻላል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements