Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መክብብ 2:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እጄ የሠራቻትን ሥራዬን ሁሉ የደከምሁበትንም ድካሜን ሁሉ ተመለከትሁ፥ እነሆ፥ ሁሉ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነበረ፥ ከፀሐይ በታችም ትርፍ አልነበረም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ሆኖም እጆቼ የሠሩትን ሁሉ፣ ለማግኘትም የደከምሁትን ድካም ሁሉ ሳስብ፣ ሁሉም ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነበር፤ ከፀሓይ በታች ምንም ትርፍ አልነበረም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ይህን ሁሉ ካደረግሁ በኋላ ያንን የሠራሁትን ነገር ሁሉ ምን ያኽል እንደ ደከምኩበት ስመለከት ከቊጥር የማይገባ ዋጋቢስ መሆኑን ተረዳሁ፤ እንዲያውም ምንም የማይጠቅምና ነፋስን እንደ መጨበጥ የሚያስቈጥር ሆኖ አገኘሁት።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እጄ የሠ​ራ​ቻ​ትን ሥራ​ዬን ሁሉ፥ የደ​ከ​ም​ሁ​በ​ት​ንም ድካ​ሜን ሁሉ ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ እነሆ፥ ሁሉ ከንቱ፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነበረ፥ ከፀ​ሐይ በታ​ችም ትርፍ አል​ነ​በ​ረም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እጄ የሠራቻትን ሥራዬን ሁሉ የደከምሁበትንም ድካሜን ሁሉ ተመለከትሁ፥ እነሆ፥ ሁሉ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነበረ፥ ከፀሐይ በታችም ትርፍ አልነበረም።

See the chapter Copy




መክብብ 2:11
13 Cross References  

ከፀሐይ በታች የተሠራውን ሥራ ሁሉ አየሁ፥ እነሆም፥ ሁሉ ከንቱ ነው፥ ነፋስንም መከተል ነው።


ከፀሐይ በታች በሚደክምበት ድካም ሁሉ የሰው ትርፉ ምንድነው?


ነገር ግን ከሃይማኖት ጋር ያለኝ ይበቃኛል ማለት ትልቅ ጥቅም የሚያስገኘ ነው፤


ሙሴም ሥራውን ሁሉ አየ፥ እነሆ ልክ ጌታ እንዳዘዘው አድርገውት ነበር፤ እንዲሁ አድርገውት ነበር፤ ሙሴም ባረካቸው።


እግዚእብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ስድስተኛ ቀን።


እነሆ፥ አሕዛብ ለእሳት እንደሚሠሩ፥ ሕዝቦችም ለከንቱነት እንደሚደክሙ ከሠራዊት ጌታ ዘንድ የሆነ አይደለምን?


አቤቱ፥ እስከ መቼ ለዘለዓለም ፊትህን ትሰውራለህ? እስከ መቼስ ቁጣህ እንደ እሳት ይነድዳል?


ጥበብንና ዕብደትን ሞኝነትንም አውቅ ዘንድ ልቤን ሰጠሁ፥ ይህም ደግሞ ነፋስን መከተል እንደሆነ አስተዋልሁ።


ለሠራተኛ የድካሙ ትርፍ ምንድነው?


ሀብት ሲበዛ የሚበሉት ይበዛሉ፥ ሀብቱን በዓይኑ ብቻ ከማየት በቀር ለባለቤቱ ምን ይጠቅመዋል?


ዘመኑን በሙሉ በጨለማ፥ በከባድ ብስጭት፥ በደዌና በቁጣ ይጨርሳል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements