መክብብ 2:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ዐይኖቼ የፈለጉትን እንዳያዩ አልከለከልኋቸውም፥ ልቤም በድካሜ ሁሉ ደስ ይለው ነበርና ልቤን ከደስታ ሁሉ አላራቅሁትም፥ ከድካሜም ሁሉ ይህ እድል ፈንታዬ ሆነ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ዐይኔ የፈለገውን ሁሉ አልከለከልሁትም፤ ለልቤም ምድራዊ ደስታን አልነፈግሁትም፤ ልቤ በሠራሁት ሁሉ ደስ አለው፤ ይህም የድካሜ ሁሉ ዋጋ ነበረ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ዐይኔ ያየውንና ልቤ የተመኘውን ሁሉ አገኘሁ፤ ለሰውነቴም የሚያስፈልገውን ደስታ ሁሉ አልነፈግሁትም፤ ደክሜ በሠራሁት ነገር ሁሉ ስለምደሰትበት እንግዲህ የእኔ ዕድል ፈንታ ይህ ነበር። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ዐይኖቼ ከፈለጉት ሁሉ አላጣሁም፥ ልቤንም ከደስታ ሁሉ አልከለከልሁትም፤ ልቤ በድካሜ ሁሉ ደስ ይለው ነበርና፤ ከድካሜም ሁሉ ይህ ዕድል ፋንታዬ ሆነ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ዓይኖቼንም ከፈለጉት ሁሉ አልከለከልኋቸውም፥ ልቤም በድካሜ ሁሉ ደስ ይለው ነበርና ልቤን ከደስታ ሁሉ አላራቅሁትም፥ ከድካሜም ሁሉ ይህ እድል ፈንታዬ ሆነ። See the chapter |