መክብብ 12:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ሰባኪውም ጠቢብ ስለ ሆነ ለሕዝቡ እውቀትን አስተማረ፥ እርሱም ብዙ ምሳሌዎችን መረመረና ፈላለገ አስማማም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ሰባኪው ጥበበኛ ብቻ አልነበረም፤ ነገር ግን ለሕዝቡ ዕውቀትንም ያስተምር ነበር። እርሱም በጥልቅ ዐሰበ፤ ተመራመረም፤ ብዙ ምሳሌዎችንም በሥርዐት አዘጋጀ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ጥበበኛው ጠቢብ ብቻ ሳይሆን ዕውቀትን ለሕዝቡ ማስተማር ቀጠለ፤ ብዙ ምሳሌዎችን መርምሮ ካጠና በኋላ በቅደም ተከተል አዘጋጀ፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ሰባኪውም ጠቢብ ስለ ሆነ ለሕዝቡ ዕውቀትን አስተማረ፥ ጆሮውም እንቆቅልሽን መረመረ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ሰባኪውም ጠቢብ ስለ ሆነ ለሕዝቡ እውቀትን አስተማረ፥ እርሱም ብዙ ምሳሌዎችን መረመረና ፈላለገ አስማማም። See the chapter |