Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መክብብ 10:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ንጉሥሽ ሕፃን የሆነ፥ መኳንንቶችሽም ማልደው የሚበሉ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ ወዮልሽ!

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 አንቺ፣ ንጉሥሽ ልጅ የሆነ፣ መሳፍንትሽም በጧት ግብዣ የሚያደርጉ ምድር ሆይ፤ ወዮልሽ!

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ሕፃን የሆነ ንጉሥና እየደገሱ ገና በማለዳ የሚሰክሩ መሳፍንት ያሉአት አገር ወዮላት

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ንጉ​ሥሽ ሕፃን የሆነ፥ መኳ​ን​ን​ቶ​ች​ሽም ማል​ደው የሚ​በሉ፥ አንቺ ሀገር ሆይ፥ ወዮ​ልሽ!

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ንጉሥሽ ሕፃን የሆነ፥ መኳንንቶችሽም ማልደው የሚበሉ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ ወዮልሽ!

See the chapter Copy




መክብብ 10:16
16 Cross References  

ወጣቶች ሕዝቤን ያስጨንቃሉ፤ ሴቶችም ይገዟቸዋል። ሕዝቤ ሆይ፤ መሪዎችህ አሳስተውሃል፤ ከመንገድህም መልሰውሃል።


የዳዊት ቤት ሆይ! ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ስለ ሥራችሁ ክፋት ቁጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣና ማንም ሳያጠፋው እንዳይነድድ፥ በማለዳ ፍርድን አድርጉ፥ የተበዘበዘውንም ከጨቋኙ እጅ አድኑ።’


ክፉዎች ሰዎችና ምናምንቴዎችም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ ሮብዓም ሕፃንና ለጋ በነበረበት ጊዜ፥ ሊቋቋማቸውም ባልቻለበት ጊዜ፥ በሰሎሞን ልጅ በሮብዓም ላይ በረቱበት።


ዮአኪንም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የስምንት ዓመት ልጅ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወርና ዐሥር ቀን ነገሠ፤ በጌታም ፊት ክፉ አደረገ።


ኢዮአቄምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አምስት ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ በአምላኩም በጌታ ፊት ክፉ አደረገ።


ኢዮአክስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ ሦስት ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወር ነገሠ።


ሴዴቅያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አንድ ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ።


አእምሮ የጐደለው መኰንን ትልቅ ግፈኛ ነው፥ ግፍን የሚጠላ ግን ብዙ ዘመን ይኖራል።


የሰነፍ ሥራ ያደክመዋል ወደ ከተማ መሄድ አያውቅምና።


አባቴ በእናንተ ላይ ከባድ የአገዛዝ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፤ እኔ ደግሞ ይኸው የአገዛዝ ቀንበር ይበልጥ እንዲከብድባችሁ አደርጋለሁ፤ ይኸውም አባቴ በአለንጋ ይገርፋችሁ ነበር፤ እኔ ግን እንደ ጊንጥ በሚናደፍ ጅራፍ በመግረፍ አሠቃያችኋለሁ!’”


Follow us:

Advertisements


Advertisements